Wednesday 29 June 2011

Sunday 26 June 2011

ደጀ ሰላም Deje Selam: ቃለ ምልልስ ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ጋር

ደጀ ሰላም Deje Selam: ቃለ ምልልስ ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ጋር: "“አዲስ ጉዳይ” መጽሔት ከመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ ጋር ያደረገው ድንቅ ቃለ ምልልስ ስለ “ተሐድሶዎች” እና በቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደቀኑት አደጋ:: (Click HERE to read in PDF )."

Saturday 25 June 2011

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተሰርታ ያለቀች ናት

"… በአሁኑ ጊዜ ያለው አገልግሎቱ እየተዳፈነ አገልጋዮቹ እየወጡ ከአገልግሎቱ ይልቅ አገልጋዮቹ እየታወቁ ነው ከወንጌሉ ይልቅ ወንጌላውያኑ … የአንድ አገልጋይ ስራ ሕዝቡን ከክርስቶስ ጋር ማገናኘት ነው አሁን …ሕዝቡ ወደእኛ ነው የሚመጣው … እግዚአብሔርን አያገኝም፡፡ አንድ ጳጳስ አንድ ሰባኪ አንድ መነኩሴ አንድ ዘማሪ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ የግል ሃሳቡን ቤተክርስቲያን ላይ ሊጭን ሳይሆን ሃሳቧን ተቀብሎ እንደ ቧንቧ ለሕዝብ ሊያዳርስ ነው፡፡ … ቤተክርስቲያንን ካህን ቤተመንግስትን ወታደር ነው የሚደፍረው …ሰው ራሱን መለወጥ ሲያቅተው ሥርዐት ለመለወጥ ይታገላል ራሱን ማደስ ሲያቅተው ሃይማኖትን ለማደስ ይታገላል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተሰርታ ያለቀች ናት ተሰርቶ ባለቀ ቤት ገብቶ መኖር እንጂ ይቀየር የማለት መብት የለህም በዝቷል ይቀነስ ረዝሟል ይጠር ተጣሟል ላቃና የሚባል ነገር የለም፡፡ ቤተክርስቲያን ሰውን ታድሳለች እንጂ ሰው ሊያድሳት አይችልም፡፡ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት አሁን ተሃድሶ ያነጣጠረባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የሚወጡ ናቸው መምህር ካህን መነኩሴና ጳጳስ የሚሆኑት እነዚህን ከያዝን በቃ ቤተክርስቲያኑን ተቆጣጠርን በሚል ሥርዐተ ትምህርቱን ጉዳት እያደረሱበት ነው፡፡ አንዳንዶቹን መምህራን ሲችሉ በጥቅም እየገዙ ደቀመዛሙርቱ ከሀገረ ስብከት ሲላኩ ሆነ ተብሎ በዚህ ደረጃ እንዲመረጡ እያደረጉ ነው … አንድ ስብከት ኦርቶዶክሳዊ የሚባለው ክርስቶስን ግንድ ቅዱሳንን ጻድቃን ሰማዕታትን ቅርንጫፍ አድርጎ ብሉይን ሓዲስን መጻህፍተ ሊቃውንት መጻህፍተ መነኮሳትን መሰረት የሥራ መጻህፍትን ቅርንጫፍ አድርጎ መስበክ ሲችል ነው ይሄን መስበክ ካልቻለ ችግር አለበት ማለት ነው፡፡ …ተሃድሶ ቤተክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ የማድረግ ስልት ነው፡፡ "



መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ስለ ተሃድሶ … (በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ሰኔ 2003)



Friday 24 June 2011

Ethiopian Orthodox Tewahedo Church In Trinidad የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በትሪኒዳድ




(Note: This video was uploaded on YouTube by on Apr 22, 2011. Here is the comment that he posted with the video.)
This is a Sunday mass at an Ethiopian Orthodox Church in Trinidad & Tobago. Almost all the people here are Trinidadians who all sing and pray in Geez. Trinidad and Tobago was the first country outside Africa and Jerusalem to receive the Ethiopian Orthodox Church. The Church arrived in Trinidad on 16th December 1952 and now exists also in Guyana, Barbados, Jamaica, Bermuda, Martinique, several North American states, Canada, Germany, Sweden and South Africa. In Trinidad and Tobago [there are] nine parishes: Arouca, Port of Spain, San Fernando, Sangre Grande, Mayaro, Point Fortin, Claxton Bay, Siparia, and Scarborough -Tobago.This one is just outside port of spain.The church was first establised by Haile Selassie I.



Sunday 19 June 2011

ጥቂት ሰለ አባቶች ከመጽሐፍ ቅዱስ - የአባቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ


መዝሙረ ዳዊት 103/ 13 "አባት ለልጆቹ እንደሚራራ እንዲሁ እግዚአብሔር ለሚፈሩት ይራራል"
መጽሐፈ ምሳሌ23 /22 "የወለደህን አባትህን ስማ"
ወደ ቆላስይስ ሰዎች  3/21 "አባቶች ሆይ፥ ልባቸው እንዳይዝል ልጆቻችሁን አታበሳጩአቸው።"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6/4 " እናንተም አባቶች ሆይ፥ ልጆቻችሁን በጌታ ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።"
መጽሐፈ ምሳሌ 4
1 እናንተ ልጆች፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፤
2 መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና፤ ሕጌን አትተዉ።
3 እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር።
4 ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር። ልብህ ቃሌን ይቀበል፤ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ።
5 ጥበብን አግኝ፤ ማስተዋልን አግኝ፤ አትርሳም፥ ከአፌም ቃል ፈቀቅ አትበል።
6 አትተዋት፥ ትደግፍህማለች፤ ውደዳት፥ ትጠብቅህማለች።
7 ጥበብ ዓይነተኛ ነገር ናትና ጥበብን አግኝ፤ ከሀብትህም ሁሉ ማስተዋልን አትርፍ።
8 ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ብታቅፋትም ታከብርሃለች።
9 ለራስህ የሞገስ አክሊልን ትሰጥሃለች፥ የተዋበ ዘውድንም ታበረክትሃለች።
10 ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ንግግሬንም ተቀበል፤ የሕይወትህም ዘመን ትበዛልሃለች።
11 የጥበብን መንገድ አስተማርሁህ፤ በቀናች ጎዳና መራሁህ።
12 በሄድህ ጊዜ እርምጃህ አይጠብብም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም።
13 ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፤ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።
14 በኃጥኣን መንገድ አትግባ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ።
15 ከእርስዋ ራቅ፥ አትሂድባትም፤ ፈቀቅ በል ተዋትም።
16 ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና።
17 የኃጢአትን እንጀራ ይበላሉና፥ የግፍንም ወይን ጠጅ ይጠጣሉና።
18 የጻድቃን መንገድ ግን እንደ ንጋት ብርሃን ነው፥ ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየተጨመረ ይበራል።
19 የኃጥኣን መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥ እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም።
20 ልጄ ሆይ፥ ንግግሬን አድምጥ ወደ ቃሌም ጆሮህን አዘንብል።
21 ከዓይንህ አታርቃት፥ በልብህም ውስጥ ጠብቃት።
22 ለሚያገኙአት ሕይወት፥ ለሥጋቸውም ሁሉ ፈውስ ነውና።
23 አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።
24 የአፍህን ጠማማነት ከአንተ አውጣ፥ ሐሰተኞቹን ከንፈሮችም ከአንተ አርቅ።
25 ዓይኖችህ አቅንተው ይዩ፥ ሽፋሽፍቶችህም በቀጥታ ይመልከቱ።
26 የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና።
27 ወደ ቀኝም ወደ ግራም አትበል፤ እግርህንም ከክፉ መልስ።"

Wednesday 15 June 2011

"የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር"


"የድንግሊቱም ስም ማርያም ነበር" 
                                             ሉቃስ 1: 27
በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ

Saturday 11 June 2011

Tuesday 7 June 2011

Protestant Vs Ethiopian Orthodox Tewahedo ክብር ለሚገባ ክብርን ስጡ

A German speaking about Tewahido Service part 1

A German speaking about Tewahido Service part 2

New Great Ethiopian Orthodox Mezmur By Zemarit Azeb.....(Tewahedo)

ተዋህዶ ሀይማኖቴ
የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ
ማህተቤን አልበስም
ትኖራለች ለዘለአለም

የግብጽን ከተሞች በደንም ገንብተናል
በመግደል ጽድቅ የለም ሞትን ግን ኖረናል
ማህተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ
እኔስ ከእነ አንገቴ ውስዱት አልሁኝ

ጴጥሮስ ተሰቀል ጳውሎስ ተሰየፈ
ተዋህዶ እያለ እረ ስንቱ አለፈ
ሌሎችም በእሳት በስቃይ አልፈዋል
ዘመን የማይሽረው ታሪክን ጽፈዋል

ፈተኛ ነንና እንዳንሆን ሐለኛ
ህዝቤ ተነቃቃ ተነሳ አትተኛ
ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን
እንዳይሆን ተረቱ
የተዋህዶ ልጆች አሁን ነው ሰአቱ


አይተን እንዳላየን ስንት አሳልፈናል
የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር
ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ክብር