የተሐድሶ መናፍቃን ስውር ሴራ ክፍል 1
The Tehadiso conspiracy part 1
ክፍል 2ን ለመመልከት እዚህ ይጫኑ Click here to watch part 2!!
በዊኒፔግ - ካናዳ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዜናዎች ብሎግ Blog of the Ethiopian Orthodox Tewahedo St Mary's and St Gabriel's Church in the City of Winnipeg, Manitoba, Canada
|
“አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ለእናንተ አድርጉ” /ሕዝ 18፥31/ |
በማሞ አየነው የሰው ልጅ ለሥጋዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴው አመች በሆነ መልኩ እግዚአብሔር ለሚያፈራርቃቸው ዘመናት ቀመር ሲያወጣ ኖሯል፡፡ ጊዜያትንም ከደቂቃ ሽራፊ እስከ ሺህ ዘመናት ድረስ ከፋፍሎ ይጠቀማል፡፡ በዚህ የጊዜ ቀመርም ትናንትን ያስረጃል፤ ዛሬን ደግሞ አዲስ ያደርጋል፡፡ በጊዜ ዑደትም ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት አልፈው ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት መጥተዋል፡፡ የዘመናት መፈራረቅ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲያደንቅ፣ መግቦቱንም እንዳይረሳ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳኑን እንዳልረሳ፣ ፍጥረቱን እንዳልዘነጋ ያመለክታል፡፡ |