Tuesday 18 October 2011

ቅድስት ድንግል ማርያም በዘይቱን - ግብጽ ከ500000 በላይ ለሆነ ሕዝብ የመታየቷ ተዓምር!!Virgin Mary appears to +500,000 people in Egypt!!

ቅድስት ድንግል ማርያም በዘይቱን - ግብጽ 
ከ500,000 በላይ ለሆነ ሕዝብ 
የመታየቷ ተዓምር!!


ከላይ ያለውን ፊልም ከተመለከቱ በዃላ ለተጨማሪ ዝርዝር መረጃ http://www.zeitun-eg.org/stmaridx.htm

Thursday 13 October 2011

Monday 10 October 2011

ዘመነ ጽጌ


ዘመነ ጽጌ
ከገነት የተሰደደውን አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩና መንበሩ ከዚያም ወደ ሚበልጥ ክብር ለመመለስ የተወለደው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ከህፃንንቱ ጀምሮ ስደትን እና መከራን ተቀብሏል፡፡

ጌታ ሲወለድ ሰብአ ሰገል «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንስግድለት መጥተናል» እያሉ በኮከብ እየተመሩ በመጡ ጊዜ በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ የሮማውያን ተወካይ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ የጌታችን ንግሥና ምድራዊ ንግሥና መስሎት መንግስቴን ሊቀማኝ ነው ብሎ ደነገጠ፡፡ ፊሪሳውያን «መሲህ ተወልዶ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ያወጣናል፡፡» ብለው ያምኑ እንደነበር ስለሚያውቅም ይህ የተፈጸመ መስሎት ጭንቀቱ በረታ፡፡ የተወለደውን ሕፃንም ለመግደል ተነሳ፡፡
ስለዚህም ሰብአ ሰገልን አስጠርቶ «ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም እንድሰግድለት ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያለበትን ንገሩኝ» በማለት በሽንገላ ተናገራቸው፡፡

Wednesday 5 October 2011