Wednesday 30 November 2011

“ታቦተ ጽዮን” ፤ “ኅዳር ጽዮን“ ፤ “አክሱም ጽዮን “ ክፍል አንድ እና ክፍል ሁለት - ዲያቆን መልአኩ እዘዘው



 ክፍል አንድ 


       የታቦተ ጽዮን መንበር -አክሱም











የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው 
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓላት አንዱ 
“ኅዳር ጽዮን” ሲሆን የሚከበረውም ኅዳር 21 ቀን ነው፡፡
የበዓሉን አከባበር ፤ ጥንተ ታሪኩን፤ ንግስት ሳባ ፤ቀዳማዊ ምኒልክና 
ሌሎችም ተያያዥ ጉዳዮችን በተከታታይ ክፍሎች እንመለከታለን፡፡ 


Sunday 27 November 2011

«ጾምን ቀድሱ» /ኢዮ.2-15/


ጾም

የሰውን ልጆች የሚወደውና ስለ እነርሱም ብሎ በገነት ያሉትን ዛፎች ሁሉ የፈጠረው እግዚአብሔር በገነት ካሉት ዛፎች መካከል አንዲቱን እንዳይበላ አዳምን አዘዘው፡፡ ይኽ አዳምን ለመጫን፣ ኃይሉን በእርሱ ላይ ለማሳየት ሳይሆን ሰው በመጾም /ባለመብላት/ እና በመታዘዝ ለሚወደው አምላኩ ፍቅሩን ይገልጽ ዘንድ ነው፡፡

ከአዳም ድቀት በኋላም በየዘመናቱ የተነሡ መንፈሳውያን ሰዎች እና ሕዝቦች በየግላቸው እንዲሁም በአንድነት /በጋራ/ ሲጾሙ፣ በጾማቸውም ሲጠቀሙ ኖረዋል /ሕዝበ እስራኤል ሙሴ፣ ኤልያስ፣ የነነዌ ሰዎች. . ./፡፡

ጌታችንም፣ በእደ ዮሐንስ ከተጠመቀ በኋላ፤ የማስተማር አገልግሎቱን ከመጀመሩ በፊት ጾሟል፡፡ 
ከዚህ ክርስቲያናዊ ትውፊት በመነሣትም ሐዋርያትና ደቀመዛሙርቱም እንዲሁ አገልግሎታቸውን ከመጀመራቸው በፊትና በአገልግሎታቸው ወቅት ይጾሙ ነበር፡፡  

YouTube BBC Christianity Ethiopian Orthodox Christianity

Wednesday 23 November 2011

ጾመ ነቢያት


እንኳን ለጾመ ነቢያት በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ

ዘመኑ ጾመ ነቢያት የተባለበት ምክንያት ነቢያት የተናገሩት ትንቢት 

ስለ ተፈጸመበት እንዲሁም በየዘመናቱ የተነሡ ነቢያት እግዚአብሔር ወደፊት ሊያደርግ ያሰበውን በእምነት ዓይን እያዩ ምሥጢር 

ተገልጦላቸው የራቀው ቀርቦ የረቀቀው ገዝፎ እየተመለከቱ ያዩትም መልካም ነገር እንዲደርስላቸው ስለ ጾሙ ስለ ጸለዩ ነው፡፡

ነቢያት ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መወለድ፣ ወደ ግብፅ ስለ መሰደድ፣ 

በባሕረ ዮርዳኖስ ስለመጠመቅ፣ በትምህርተ ወንጌል ጨለማውን 

ዓለም ስለ ማብራቱ፣ ለሰው ልጆች ድኅነት ጸዋትወ መከራ 

ስለመቀበሉና ስለ መሰቀሉ፣ ስለ ትንሣኤው፣ ስለ ዕርገቱና 

ስለ ዳግም ምጽአቱ ትንቢት ተናግረው አላቆሙም፤ 

ለአዳም የተሰጠው ተስፋ ተገልጦላቸው ለተናገሩት 

ትንቢት ፍፃሜ እንዲያደርሳቸው ፈጣሪያቸውን 

ተማፀኑትም እንጂ፡፡ በየዘመናቸው «አንሥእ ኃይለከ፣ 

ፈኑ እዴከ፤ ኃይልህን አንሳ እጅህንም ላክ» እያሉ ጮኹ፡፡ 

በጾምና በጸሎት ተወስነውም ሰው የሚሆንበትን ጊዜ በቀናት፣ በሳምንታት፣ በወራትና በዓመታት ቆጠሩ፡፡ 

ለምሳሌ ነቢዩ ኤርምያስ ስለ ሥጋዌው ትንቢት በተናገረ 

በ446 ዓመት ጌታችን ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ

 ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኗል፡፡


Sunday 20 November 2011

Zemarit Alem Zegeye


Our sister Zemarit Alem Zegeye - beloved daughter of the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church, whose life was dedicated to the service of our Lord, Savior and God Jesus Christ has departed to join the Saints in Heaven. Her body has been laid to rest in her native Kombolcha town - near the City of Harar. A memorial service has been conducted at her Debre Genet St Mary's and St Gabriel's church in Winnipeg, Canada today - November 20, 2011. Alem has upheld her purity and was living in Holy Communion. She was patient and soft spoken but fiercely loyal to her Orthodox Tewahedo Christian religion. She served the church with dedication, vigour and energy. We will all miss you dear Alem! You have been loyal to the Orthodox Tewahedo faith to your last breath. Your life is a model for us! We all love you. We pray that the Lord give us the strength to stand firm like you did in the one and true faith - Tewahedo - till the last second of our life. We pray that the Lord give us the strength to abhor sin and live in sanctity and Holy Communion like you did.
  
Winnipeg loves you dear Alem!
Debre Genet - your beloved Church will always remember you and honour you!
Rest in peace Alem dear!!