Saturday 29 December 2012

እኛ የምናመልከው አምላክ ኪሚነደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፡፡ ት.ዳን.3፥17



ታኅሣሥ 18 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ኀይለ ኢየሱስ ቢያ

ST. Gebrealeንጉሡ ናቡከደነጾር በዱራ ሜዳ ላቆምኩት የወርቅ ምስል ካልሰገዳችሁ ከእጄ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው? ብሎ በኀይልና በዛቻ በጠየቃቸው ጊዜ ሠለስቱ ደቂቅ በልበ ሙሉነት፥ በፍጹም እምነት፥ መልስ የሰጡበት ኀይለ ቃል ነው፡፡ ከኀይለ ቃሉ ቅዱስ ዳዊት አመንኩ በዘነበብኩ /በተናገርሁት አመንሁ፤ እንዳለ መዝ.115፥1 ፍጹም እምነታቸውንና ታማኝነታቸውን፣ ጽናታቸውን እንረዳለን፡፡ ዛሬ የምናከብረው የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል በዓል ሠለስቱ ደቂቅን ከባቢሎን እሳት ያዳነበት ነው፡፡ ታሪኩ የተፈጸመው በብሉይ ኪዳን ዘመን ከ605-562 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በነገሠው በናቡከደነጾር ዘመን ነው፡፡

Friday 28 December 2012

ታኅሣሥ ገብርኤል


ዲያቆን መልአኩ እዘዘው

ገብርኤል ማለት “እግዚእወገብር” -የእግአብሔር አገልጋይ ማለትነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበትበዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፡ ማንፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹጊዜ “የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅበያለንበት ጸንተን እንቁም”  ብሎያረጋጋቸው መልአክ ነው። 

Thursday 29 November 2012

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽዮን


ኅዳር 20/2004 ዓ.ም
ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ የአምልኮ ሥርዐታትን ይፈጽሙበት ዘንድ የምስክሩን ድንኳን፣ የቃል ኪዳኗ ታቦትንና ለአምልኮ ሥርዐቱ ማከናወኛ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትን እንዲሠሩ በሙሴ በኩል ታዘው ነበር፡፡ ከቃል 3p-03ኪዳኗ ታቦት ውስጥም በእግዚአብሔር ጣት ዐሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት የሕጉ ጽላት፣ አርባ ዓመት ሙሉ እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ የተመገቡትን መና የያዘች መሶበ-ወርቅ፣ አሮን ለክህነት አገልግሎት ስለመመረጡ ምስክር የሆነችው ለምልማና ፍሬ አፍርታ የተገኘችው የአሮን በትር ይገኙባታል፡፡(ዕብ.9፡4)

"ስለ ጽዮን ዝም አልልም" A video sermon on Tsion by Kesis Nehmia getu

Tuesday 27 November 2012

እምነ ጽዮን - እናታችን ጽዮን


ዲያቆን መልአኩ እዘዘው
እንኳን ለኅዳር ጽዮን በሰላም አደረሳችሁ
በቅዱሳት መጻሕፍት ጽዮን የሚለው ቃል ተደጋግሞ በነቢያቱ ተነግሯል፡፡ ሆኖም የጽዮን ትርጉም እንደተነገረበት ዐውደ ትንቢት እንደተሰበከበት መዋዕለ ትምህርት ምስጢሩ ይለያያል፡፡
ድንግል ማርያም ምስለ ፍቁር ወልዳ
 ታቦተ ጽዮን በፈቃደ እግዚአብሔር በነቢዩ ሙሴ አማካኝነት ለሰው ልጆች ተሰጥታ እስራኤላውያን ሲባረኩባት፣ መሥዋዕታቸውን ሲያቀርቡባት ከእግዚአብሔር ሲታረቁባት ኖረዋል፡፡ከአራት ሺሕ ሦስት መቶ ሃያ ሰባት ዓመተ ዓለም (4327 ዓ.ዓ.) ጀምሮ ለአርባ ዓመታት ያህል እስራኤላውያንን በክህነት ያገለግል የነበረው ካህኑ ዔሊ ዕድሜው ሲገፋ ሁለት ልጆቹን ጠርቶ ምሉዕና ዱግ /ዋናና ምክትል/ አድርጎ ሾማቸው፡፡

Thursday 22 November 2012

ጾመ ነቢያት


በዲ/ን አሻግሬ አምጤ
ቀን: ህዳር 14/2004ዓ.ም.
ክርስቲያኖች ከእግዚአብሔር በጸጋ እንደተወለዱ በማመን ለእግዚአብሔር ያላቸውን ፍቅር ከሚገልጡባቸው ነገሮች አንዱ ጾም ነው፡፡ ጾም ፍቅረ መብዓ ከመሆኑ በተጨማሪ ታዛዥነትንና የገቡትን ቃል ኪዳን ጠባቂነትንም ማሳያ ነው፡፡ የሰው ልጅ በእግዚአብሔር አርአያ ተፈጥሯአል፡፡ ኃጢአት ሠርቶ የእግዚአብሔር አርአያነቱን ቢያጠፋውም እግዚአብሔር ግን በአርአያው ሲፈጥረው ምን ያህል እንደሚወደው ማረጋገጫ ስለነበር በኃጢአት ሲወድቅም እንደወጣ ይቅር ሳይል ሊፈልገው መጣ፡፡ እግዚአብሔር የሰውን ልጅ ሊፈልግ የመምጣቱ ተስፋ የተነገረበትንና ሱባኤ የተቆጠረበትን ዕለት ለማየት በመናፈቅ ከቀረበው መሥዋዕት አንዱ ጾም ነበር፡፡

Wednesday 21 November 2012

“በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ በፊትህ መልአክ እሰዳለሁ፤” ዘፀ.33፥1-3

ኅዳር 11 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ኢዮብ ይመኑ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

mikealeበረሃብ ስደት ምክንያት ከከነዓን ወደ ግብፅ የመጡት ሰዎች ከዮሴፍ ጋር ሰባ ነበሩ፡፡ /ሐዋ.7/ በግብፅም በአባታቸው በያዕቆብ ምርቃት ቁጥራቸውም እጅግ በዛ፡፡ ይህም የቁጥራቸው መብዛት ከ1280-1445 ቅድመ ልደተ ክርስቶስ የተነሣውንና ዮሴፍን የማያውቀውን ንጉሥ አስፈራው፡፡ /ዘፀ.1፥8/ ንጉሡም ጠላት ይሆኑብናል ያም ባይሆን ጠላት ቢነሳብን አብረው ይወጉናል በሚል ፍርሃት አገዛዝ በማጥናት በቀን በሌሊት በከባድ ሥራ እየጠመደ በጭካኔ ጡብ እያስገነባ ፊቶም፣ ራምሴ፣ ዖንን የተባሉ ታላላቅ ከተሞችን እያሠራ ኖራ እያስወቀጠ ጭቃ እያስረገጠ በሥራ ደክመው ልጅ እንዳይወልዱና ጉልበታቸውን እየደከመ በጅራፍ አየገረፈ መከራ አጸናባቸው፡፡

Monday 12 November 2012

ዘመነ አስተምህሮ


ኅዳር 6/2004 ዓ.ም
በቤተ ክርስተያናችን የዘመን አቆጣጠር /አከፋፈል/ መሠረት ከኀዳር 6 ጀምሮ እስከ ታኀሣሥ 13 ድረስ ያለው ወቅት ዘመነ አስተምህሮ ይባላል፡፡

መሀረ ማለት ይቅር አለ ማለት ሲሆን፤ ዘመነ አስተምህሮ ማለት ይቅርታ የመጠየቅ /የምልጃ/ ዘመን ማለት ነው፡፡ ዘመኑ ቤተ ክርስቲያን ስለ ልጆቿ ይቅርታ የምትጠይቅበት፤ ምዕመናንንም ስለ በደላቸው ይቅርታ የሚጠይቁበት፤ ስለዚህም በስፋት ትምህርት የሚሰጥበት ዘመን ነው፡፡
በዚህ ዘመን ያሉት አምስት እሑዶችና በእነዚህ እሑዶች የሚጀምሩት ሳምንታት አስተምህሮ፣ ቅድስት፣ ምኩራብ፣ መጻጉዕ፣ እና ደብረ ዘይት በመባል ይጠራሉ በየሳምንቱ ቤተ ክርስቲያን የምታቀርበውን ትምህርት በየጊዜው እናከብራለን የመጀመሪያውን ሳምንት /የአስተምህሮ/ ትምህርት እነሆ: -

Sunday 21 October 2012

ጾመ ጽጌ

ዲያቆን መልአኩ እዘዘው












የጾም ትርጓሜ
የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል፡- ጾምሰ ተከልአተ ብእሲ እመብልዕ በጊዜ ዕውቅ በውስተ ሕግ - ጾምስ በታወቀው ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ አንድም ጾም ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ ይህም ኃጢአቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥራም ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ነው፡፡ ፍት.ነገ.ፍት. መ. አንቀጽ 15564፡፡ በዚህ መሠረት ጾም ማለት ከጥሉላተ መባልዕት /ሥጋ ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል እንዲሁም የአልኮል መጠጦች/ መታቀብ ነው፡፡

ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ ማቴ 2፥13

Friday 5 October 2012

ዘመነ ጽጌ

መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ክረምቱ አልፎ  በጋ ሲተካ ተራውንም ለዘመነ መፀው ሲያስረክብ የመጀመሪያው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ያለው ወቅት ዘመነ ጽጌ sidet2ይባላል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠራር በዘመነ ጽጌ ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚደርሰው ስብሐተ እግዚአብሔር የሚቆመው ማኅሌቱ ደግሞ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ ይጠራል፡፡ በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰው ማኅሌተ ጸጌ እየተባለ የሚጠራው መልክ መሰል ድርሰትም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ እየተቃኘ አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜም ይኸው ዘመነ ጽጌ ነው፡፡

Wednesday 26 September 2012

"ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥ ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው::" መዝ 59:4

ቅዱስ መስቀል ፍቅር ነው

መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
አባ ዘሚካኤል

meskele 1ወሶበ ርእዮሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእሙ ወለረድኡ ዘያፈቅር ይቀውሙ፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደውን ደቀ መዝሙርና እመቤታችንን ከእግረ መስቀል ቁመው ባያቸው ጊዜ፣ ወይቤላ ለእሙ ኦ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ፤ አንቺ ሆይ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ አላት፡፡ ውሉድኪ ሲል ነው በዮሐንስ እኛን ለርስዋ መስጠቱ ነውና፡፡ ወይቤሎ ለውእቱኒ ረድ ነያ እምከ፣ ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ታጽናህ አለው እምክሙ ሲል ነው፡፡ በዮሐንስ እርስዋን ለኛ መስጠቱ ነውና፡፡(ዮሐ. 19: 26-27)

Monday 24 September 2012

መስቀሉ የት ነው ያለው?

ከዳንኤል ክብረት

(ምንጭ- ስንክሳር- የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ)



በእምነትታሪክ ውስጥ የታሪክ፣የአርኬዎሎጂ እናየቅርስ ጥናት ሰዎችንያስጨነቁ ሁለትጥያቄዎች አሉ፡፡ ታቦተጽዮን እና ጌታየተሰቀለበት መስቀልየት ነው ያሉት?የሚሉት ጥያቄዎች፡፡እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አሰሳዎች፣ ቁፋሮዎች፣ መዛግብትን የማመሳከር ሥራዎች፣ አሉ የተባሉየይዞታ ጥያቄዎችን የመመርመር ፍተሻዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን የዓለም ቅርሶች መናኸርያ የሆነችው ኢትዮጵያ ሁለቱን በተመለከተ ለዓለም የምትገልጣቸው ነገሮች አሏት፡፡

Saturday 15 September 2012

መስቀልና እመቤታችን


በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ (ምንጭ፡ ደቂቀ ናቡቴ ብሎግ)
  • መግቢያ 
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ለእያንዳንዱ የቤተሰብእ አባል የራሱ የሆነ ቦታ ወይም ደረጃ አለው፡፡ እናት ያላት ቦታ አለ፡፡ አባት ያለው ቦታ አለ፡፡ ልጆች ያላቸው ቦታ ደግሞ ይኖራል፡፡ የልጆች ቦታ እንኳን እንደ እድሜያቸውም ሆነ እንዳላቸው የትምህርት፣ የሥራና የሥነ ምግባር ሕይወት የተለያየ ነው፡፡ የታላቅ ልጅ ቦታ ከታናሽ ይለያል፡፡
ይህ ዓይነቱ የመዋቅር ልዩነት በየትም ቦታ ይታያል፡፡ በወታደር ቤት ይህ ልዩነት አለ፡፡ በቢሮና በማናቸውም መድረክ ይህ ዓይነቱ ልዩነት የተጠበቀ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በአንድ ሰው ውስጥም በአካል ብልቶች መካከል ይህ ልዩነት አለ፡፡ ልዩነቱ የኃላፊነት፣ የወሳኝነትና የአስፈላጊነት መጠንን ይገልጣል፡፡ ይህን ልዩነት ተከትሎ የሚመጣ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ይኸውም የክብር ልዩነት ነው፡፡

Monday 10 September 2012

“አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ለእናንተ አድርጉ” /ሕዝ 18፥31/


በማሞ አየነው
የሰው ልጅ ለሥጋዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴው አመች በሆነ መልኩ እግዚአብሔር ለሚያፈራርቃቸው ዘመናት ቀመር ሲያወጣ ኖሯል፡፡ ጊዜያትንም ከደቂቃ ሽራፊ እስከ ሺህ ዘመናት ድረስ ከፋፍሎ ይጠቀማል፡፡ በዚህ የጊዜ ቀመርም ትናንትን ያስረጃል፤ ዛሬን ደግሞ አዲስ ያደርጋል፡፡ በጊዜ ዑደትም ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት አልፈው ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት መጥተዋል፡፡ የዘመናት መፈራረቅ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲያደንቅ፣ መግቦቱንም እንዳይረሳ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳኑን እንዳልረሳ፣ ፍጥረቱን እንዳልዘነጋ ያመለክታል፡፡

ዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ እና ቅዱስ ድሜጥሮስ ተካሌ ወይን



ማቴዎስ ወንጌላዊ
እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ 2005 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ  
ዕንቁጣጣሽ
አዲሱ ዓመት የንስሐ ፤ የቅድስና ፤ የደስታ ፤ የፍስ ፤ የፍቅር ያድርግልን


ድሜጥሮስ መስታወት ነው-በመስታወት ከዓይን ጉድፍ ከጥርስ እድፍ አይተው እንደሚያጸዱበት ሁሉ ባሕረ ሐሳብንም የተማረ ሰው ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ምጽአት ድረስ የሚሆነውን ቁጥር ያውቃልና፡፡ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ አንድም ሐሳብ ባሕር ይለዋል ዘመን ያለው ቁጥር ሲል ነው፡፡

Friday 17 August 2012

ምሥጢረ ደብረታቦር


አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ  ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንምኤልያስ እንሥራ  ›      
 ቅዱስ ጴጥሮስ

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው
           ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።

Wednesday 8 August 2012

ጾመ ፍልሰታ


ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ፈጣሪያችን ጾሙን የበረከት፣ የረድኤት የንስሓ ያደርግልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ ንስሓ ገብተን፣ ጾመን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን ሕይወት እንድናገኝ የፈጣሪያችን ቸርነቱ አይለየን! አሜን

ጾም፡- መተውን መከልከልን መታቀብን፣ መታረምን የሚገልጥ የግብር ስም ነው፡፡

kidaseየቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓትና የሕግ መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት በ15ኛው አንቀጹ መግቢያ ላይ “ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው፡፡ በደሉን ለማስተሥረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱን ወዶ ሕጉን ለሠራለት እየተታዘዘ የፈቲዉን ኀይል ያደክምበት ዘንድ ለነባቢትም ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ፤” በማለት የጾምን ምንነትና ጥቅም አጠር አድርጎ ያብራራል፡፡

Tuesday 7 August 2012

ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር


እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ
















ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪመካነ ፍሥሐ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባህርይ ዘተነድቀ ፤ ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ

እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ፡፡ ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቊ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል፡፡
               መልክአ ማርያም

Wednesday 25 July 2012

"ደጉ መልአክ ገብርኤል" zemari tewodros yosef

ቁልቢ ገብርኤል



ቁልቢ ገብርኤል



ዲያቆን መልአኩ እዘዘው

 ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461/ርቀት ላይ በምዕራብ ሐረርጌሀበገረ ስብከት
 ጋራ ሙለታ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ የዚህን ደብርአመሠራረት በተመለከተ 
በብዙ ሊቃውንትየሚተረከው የሚከተለው ነው::በዘጠነኛው //ዮዲት ጉዲት
ተነሥታ አብያተ ክርስቲያናትንስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና
መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአኩስምና በአከባቢዋ የነበሩ 
ታቦታትንና ንዋያተቅዱሳትን በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡


Saturday 21 July 2012

ቤተክርስቲያን እንዴት ተመሠረተች ?

ዲያቆን መልአኩ እዘዘው








ስለ ክርስትና ሃይማኖት ስለ ቤተክርስቲያን በምንናገርበት ጊዜ ሁሉ ትዝ የሚለንና የምናስተውለው የመጀመሪያው ሰው የአዳም ሁኔታ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን እግዚአብሔር የሁላችንን አባት አዳምን በአርአያውና በመልኩ ከፈጠረው በኋላ ባረከው፡፡

Wednesday 11 July 2012

ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ጳውሎስ

ዲያቆን ታደሰ ወርቁ
እነዚህ ሁለት ቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስት ቤተክርስቲያናችን አዕማድ ናቸው፡፡ በመሠረትነት በአጸኗት ቤተክርስቲያን ያላቸው የክብር ሥፍራ ላቅ ያለ ነው፡፡ ይህ የሆነው እንዲሁ አይደለም፡፡ ለቤተክርስቲያንና በቤተክርስቲያን የፈጸሙት አገልግሎት በዚህም የተቀበሉት ሰማዕትነት ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍትም ይህን መልካም የሆነውን ታሪካቸውን ለእኛ አርአያነት በሚሆን መልኩ ከትበውልናል፡፡ እኛም ለአርአርያነት በሚሆን መልኩ የእነዚህን ደጋግ ሁለት ቅዱሳን አባቶች ታሪክ፣ ዕውቀትና መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ከዚህ በመቀጠል አቅርበናል፡፡
1. ሁለቱ ሐዋርያት ሲጠሩ የነበሩበት ሕይወት
ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተ ሳይዳ ሲወለድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳዉሎስ ደግሞ በጠርሴስ ከተማ ተወለደ፡፡