Friday 17 August 2012

ምሥጢረ ደብረታቦር


አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ  ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንምኤልያስ እንሥራ  ›      
 ቅዱስ ጴጥሮስ

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው
           ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።

Wednesday 8 August 2012

ጾመ ፍልሰታ


ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ፈጣሪያችን ጾሙን የበረከት፣ የረድኤት የንስሓ ያደርግልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ ንስሓ ገብተን፣ ጾመን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን ሕይወት እንድናገኝ የፈጣሪያችን ቸርነቱ አይለየን! አሜን

ጾም፡- መተውን መከልከልን መታቀብን፣ መታረምን የሚገልጥ የግብር ስም ነው፡፡

kidaseየቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓትና የሕግ መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት በ15ኛው አንቀጹ መግቢያ ላይ “ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው፡፡ በደሉን ለማስተሥረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱን ወዶ ሕጉን ለሠራለት እየተታዘዘ የፈቲዉን ኀይል ያደክምበት ዘንድ ለነባቢትም ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ፤” በማለት የጾምን ምንነትና ጥቅም አጠር አድርጎ ያብራራል፡፡

Tuesday 7 August 2012

ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር


እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ
















ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪመካነ ፍሥሐ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባህርይ ዘተነድቀ ፤ ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ

እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ፡፡ ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቊ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል፡፡
               መልክአ ማርያም