Sunday 21 October 2012

ጾመ ጽጌ

ዲያቆን መልአኩ እዘዘው












የጾም ትርጓሜ
የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል፡- ጾምሰ ተከልአተ ብእሲ እመብልዕ በጊዜ ዕውቅ በውስተ ሕግ - ጾምስ በታወቀው ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡ አንድም ጾም ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡ ይህም ኃጢአቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥራም ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ነው፡፡ ፍት.ነገ.ፍት. መ. አንቀጽ 15564፡፡ በዚህ መሠረት ጾም ማለት ከጥሉላተ መባልዕት /ሥጋ ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል እንዲሁም የአልኮል መጠጦች/ መታቀብ ነው፡፡

ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ፡፡ ማቴ 2፥13

Friday 5 October 2012

ዘመነ ጽጌ

መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም.
በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
ክረምቱ አልፎ  በጋ ሲተካ ተራውንም ለዘመነ መፀው ሲያስረክብ የመጀመሪያው ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ያለው ወቅት ዘመነ ጽጌ sidet2ይባላል፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አጠራር በዘመነ ጽጌ ማለትም ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 6 ባለው ጊዜ ውስጥ የሚደርሰው ስብሐተ እግዚአብሔር የሚቆመው ማኅሌቱ ደግሞ ማኅሌተ ጽጌ ተብሎ ይጠራል፡፡ በአባ ጽጌ ድንግል የተደረሰው ማኅሌተ ጸጌ እየተባለ የሚጠራው መልክ መሰል ድርሰትም በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ እየተቃኘ አገልግሎት የሚሰጥበት ጊዜም ይኸው ዘመነ ጽጌ ነው፡፡