Sunday 22 April 2012

Our kids and their model


Our kids love Aba. For most of them he is their model. 
They "want to be like him when they grow up". 





የትንሣኤው ትርጉም በዓሉና አከባበሩ


ከሊቀ ትጉሃን ኀ/ጊዮርጊስ ዳኘ
በጠ/ቤተ ክህነት የዕቅድና ልማት መምሪያ ምክ/ሓላፊ
- «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡

- መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡

- «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡

- «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡

Saturday 14 April 2012

ትንሣኤ ዘክርስቶስ


፩፦ ትንሣኤ ዘክርስቶስ፤

(ይህ ጽሑፍ ለ፪፼፪ ዓም ትንሣኤ በማኅበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ላይ ወጥቶ የነበረ ነው።)

ጌታችን  አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡ ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው  ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል።

"FASIKA" Easter 1 TTEOTV

የትንሣኤ ትምሕርት በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ


"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡"
“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ” ይህ ቃል የትንሣኤው የምሥራች ለምእመናን የሚታወቅበት ነው የሚቀድስ ካህን፣ ሰባኪ በዘመነ ትንሣኤ ከስብከቱ አስቀድሞ በዚህ ቃል የክርስቶስን መነሣት ያውጃል፡፡ የሚቀድሰው ካህንም በኪዳን ጊዜ ህዝቡን ከመባረኩ አስቀድሞ ይህንኑ ቃል ይናገራል ሰላምታ የሚቀባበሉ ምእመናንም ሰላምታ ከመስጠት አስቀድሞ ይህን ቃል በመናገር የትንሣኤውን አዋጅ ማወጅና መመስከር ይገባቸዋል፡፡ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን አደረሳችሁ!!!

Thursday 12 April 2012

"ሞት በሞት ሞተ" በዲያቆን ዳንኤል ክብረት

The Passion of the CHRIST ( FULL MOVIE)

ኪሪያላይሶን Kiralayson

ዘበእንቲአሃ (የስቅለት መዝሙር) zebe'entiaha

አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል



አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል

(ምንጭ - ስንክሳር- የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ)



               በሰሙነ ሕማማት ጠቅለል ባለ መልኩ የምናስባቸው የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማት አሥራ ሦስት ናቸው፡፡ እነርሱም አሥራ ሦስቱ ሕማማተ መስቀል ይባላሉ፡፡ ለክርስቲያኖች እነዚህን ሕማማተ መስቀል ማወቅና ዘወትር ማሰብ ተገቢ በመሆኑ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡


ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 1 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 1

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 2 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 2

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 3 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 3

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 4 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 4

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 5 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 5

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 6 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 6

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 7 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 7

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 8 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 8

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 9 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 9

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 10 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 10

ሆሣዕና ፳፻፬ በኢኦተቤ ዊኒፔግ ካናዳ ቪዲዮ 11 Hosanna 2012 at the EOTC in Winnipeg Canada, video 11

Wednesday 11 April 2012

ጸሎተ ሐሙስ



                  ጸሎተ ሐሙስ
በሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ
ጸሎተ ሐሙስ ነቢያት በሀብተ ትንቢት በመንፈሰ ትንቢት ‹‹እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት›› /መዝ. 117፥24/ በማለት ትንቢት የተናገሩላት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ትላልቅ የተባሉ ምሥጢራት የተፈጸሙባት ዕለት ናት፡፡


Sunday 8 April 2012

Semune himamat - Part 1 of 6

Semune himamat - Part 2 of 6

Semune himamat - Part 3 of 6

Semune himamat - Part 4 of 6

Semune himamat - Part 5 of 6

Semune himamat - Part 6 of 6

ሥርዐተ ሰሙነ ሕማማት


                                ሥርዐተ ሰሙነ ሕማማት

(ምንጭ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002 :: 
ስንክሳር-  የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ )

ሥርዐት ምንድን ነው?

ወንድሞች ሆይ፡ ከእኛ እንደተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሔድ 
ወንድም ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። 
በእናንተ ዘንድ ያለሥርዐት አልሔድንምና። “ (2 ተሰ. 3 6)

ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት


ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት

(ምንጭ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002 :: 
ስንክሳር-  የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ )

በዐቢይ ጾም ከሠርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ሌሊት 
ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡ 
ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡ 
በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ 
ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፣ 
አክፍሎት፣ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጣብ፣ ጉልባን እና 
ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡ 


Wednesday 4 April 2012

"Hosanna" TTEOTV

ሆሳዕና - አጭር ትምሕርታዊ ቪዲዮ

ሆሣዕና በዲ/ን ቀለመወርቅ ሚደቅሳ


Hosahna.JPG
በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት የዐቢይ ጾም ሳምንታት የየራሳቸውን ምክንያት መሠረት በማድረግ ልዩ ልዩ ስያሜዎችን ይዘው እናገኛቸዋለን፡፡ በዚህም መሠረት የሰሙነ ሕማማት ዋዜማው ሰንበት ሆሣዕና ተብሎ ይታወቃል፡፡ በዚህም አምላክ ወልደ አምላክ ሥግው ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ የጽድቅ የትሕትና እና የፍቅር ንጉሥ ሆኖ ወደ ኢየሩሳሌም የገባበት ነው፡፡ /ማቴ.21÷1፣ ማር.11÷1፣ ሉቃ.19÷23፣ ዮሐ.12÷12/