Wednesday 16 May 2012

ቅኔ በቤተ ክርስቲያን (ክፍል 1) - በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ



              ቅኔ በቤተ ክርስቲያን 
በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ (ክፍል 1)

ቅኔ በቤተ ክርስቲያን (ክፍል 2)- በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ



                 ቅኔ በቤተ ክርስቲያን 
በመጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ (ክፍል 2)

Thursday 10 May 2012

Mehamud Ahmed - Yom Fisha Kone Be Inte Lideta Lemariam


ማህሙድ አህመድ (ሃብተ ወልድ) ፡ 
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

Tuesday 8 May 2012

የቀኝ ዐይን - ድንግል ማርያም



ሚያዝያ 28/2003ዓ.ም
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም በጊዜ  ምንዳቤ ወአጸባ ለዐይን እምቀራንባ፤ አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ፤ በኩሉ ኅሊናሃ ወበኩሉ አልባባ፤ዘኢታፈቅረኪ ነፍስ ትሠሮ እምሕዝባ፡፡

lidetaleMariam

የነገረ ማርያም ሊቅ(Marian Doctor)እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እመቤታችንን በብዙ ምሳሌ እየመሰለ፣ እየተረጎመና እያመሰጠረ ብዙ ጊዜ አመስግኗታል፡፡ ምንም እንኳን እኛ የምናውቀው የምስጋና ድርሰቱ ለጸሎት የምንጠቀምበት ውዳሴ ማ��ን በእርሷ አዘጋጀና መንፈሷን ጽሩይ አደረገ፤አሳቦቿን አጠራ፣ኅሊናዋንም ንጹሕ አደረገ፤የድንግልናዋንም ክብር አበራው ››/Hymns on the Church, 36, 1-2/፡፡ ሊቁ በዚሁ ድርሰቱ ውስጥ ሌላ ቦታ ላይ ደግሞ፤ ‹ለዚህ ዓለም ሁለት ዐይኖች ተሰጡት፤ ማየት ያልተቻላት የግራ ዐይን ሔዋን ስትሆን፣ የምታበራው የቀኝ ዐይን ደግሞ (እመቤታችን) ማርያም ናት፡፡በማታየው በጨለማዋ ዐይን ምክንያት መላው ዓለም ጨለመ፤ ስለዚህም ሰዎች በጨለማ ጥላ ውስጥ ሆነው ሲዳብሱ ያገኙት ሁሉ አምላክ ፣ ሐሰቱም እውነት መሰላቸው፡፡ነገር ግን ዓለም እንደገና በሌላ ዐይኑ ባበራና (ባየና) ሰማያዊው ብርሃንም በዚች ዐይን ሰሌዳ ውስጥ ባንጸባረቀ ጊዜ ሰዎችም ቀድሞ ያገኙትን(ያመለኩትን) የኑሮአቸው ውድቀት(የባሕርያቸው መጎስቆል) መሆኑን ተረድተው ወደ ማንነታቸው ተመለሱ (አንድነታቸውን አገኙ)›› ይላል /Ibid, 37, 5-7/::

“መሠረታቲሃ ውስተ አድባር ቅዱሳን፡- መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው” /መዝ.86፥1/


ሚያዚያ 30/2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኩኖአምላክ
ይህ ቃል የእመቤታችንን አያቶቿን የቀደሙ ወላጆቿን ንጽሕና፣ ቅድስና፣ ክብር አስመልክቶ ቅዱስ ዳዊት የተናገረው የምስክርነት ቃል ነው፡፡ ይህ ምስክርነት አካላዊ ቃል እግዚአብሔር ወልድ ለኩነተ ሥጋ የመረጣት ቅድስት ድንግል ማርያም ወላጆቿ ንጹሐን፣ ቅዱሳን መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሲመላለስ፡- “መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬን ያፈራል፤ ክፉ ዛፍም ክፉ ፍሬን ያፈራል፡፡ መልካምም ዛፍ ክፉ ፍሬን ማፍራት፥ ክፉ ዛፍም መልካም ፍሬን ማፍራት አይችልም” ማቴ.7፥17-18፡፡ በማለት እንደተናገረው እመቤታችን ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የተገኘችባቸው ወላጆቿ ሁሉ ቅዱሳን ንጹሐን፣ እግዚአብሔርን የሚወዱና የሚያከብሩ መሆናቸውን ልብ ይሏል፡፡ ለመሆኑ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የዘር ሐረግና የትውልድ ታሪኳ ምን ይመስላል?
በነገረ ማርያም ሰፍሮ ከምናገኘው ሰፊ ታሪክ ከፊሉን እንዲህ አቅርበነዋል፡፡ መልካም ንባብ!

Lideta Le Mariam 2004/2012 Wereb - Winnipeg - CANADA

Z/T Werknesh Haylu - Zim Atbelu and Yom Fiseha Kone- Winnipeg, CANADA

Saturday 5 May 2012

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል አደረሳችሁ!!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም


«መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው» /መዝ. ፹፮፥፩/





የዛሬ 2019 ዓመታት ወደኋላ ዘወር ብለን ስንመለከት ታሪክን የሚለውጥ አንድ ድንቅ ክስተት መፈጸሙን እናገኛለን። ይህም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት ነው። ልበ አምላክ የተባለ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት «መሠረቶቿ የተቀደሱ ተራሮች ናቸው» ያላትም እርሷን ነው። /መዝ. ፹፮፥፩/። የተቀደሱ ተራሮች የተባሉ የእመቤታችን ወላጆችና ቅድመ አያቶች ሲሆኑ እኒህም እነ ኖኅ እና አብርሃም ናቸው። እነዚህ ሁሉ ቅዱሳን ናቸውና። ኢያቄምና ሐናም ከተቀደሱት ተራሮች መካከል ሲሆኑ የእመቤታችን አባትና እናትም ናቸው። ሁለቱም በተቀደሰ ጋብቻ ጸንተው ቢኖሩም መካን በመሆናቸው ያዝኑ ነበር። ይሁንና በስተእርጅና እግዚአብሔር ልጅ እንዲሰጣቸው ብፅዓት ገቡ። ብፅዓቱም «ወንድ ብንወልድ ወጥቶ ወርዶ አርሶ ቆፍሮ ነግዶ አትርፎ ይርዳን አንልም፤ ለቤተ እግዚአብሔር ጠባቂ አገልጋይ ይሁን እንጂ፣ ሴትም ብንወልድ እንጨት ሰብራ እንጀራ ጋግራ ውሃ ቀድታ ወፍጮ ፈጭታ ትርዳን አንልም፤ ለቤተ እግዚአብሔር ውሃ ቀድታ መሶበ ወርቅ ሰፍታ ትኑር እንጂ» የሚል ነው። እግዚአብሔርም የነገሩትን የማይረሳ የለመኑትንም የማይነሳ ቸር አምላክ ነውና ብፅዓታቸውን ፈጸመላቸው። በተቀደስ ጋብቻ ንጽሕት ቅድስት ልጅ አገኙ። ይህንንም የልደቷን ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በደስታ ታከብረዋለች።



ስለእመቤታችን ቅዱሳን መጻሕፍት ምን ይላሉ?