Sunday 13 October 2013

የሰበካው መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባዔ አስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ


የሰበካው መንፈሳዊ ጠቅላላ ጉባዔ አስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ
የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን በዊኒፔግ ሕገ-ደንብ ቁጥር 1 አንቀጽ 14.01(C) አንቀጽ 19.04 እና አንቀጽ 19.06 በሚደነግጉት መሠረት
1/ እሑድ ኖቨምበር 3 ቀን ከሰዓት በኋላ 3.00 ኤም ጀምሮ የሰበካው ጠቅላላ ጉባዔ አስቸኳይ ስብሰባ ይደረጋል
2/ የስብሰባው ቦታ 353 ማውንቴን አቬኑ ይኾናል።
3/ የስብሰባው አጀንዳ ወቅታዊ የኾኑ የቤተክርስትያናችን ጉዳዮች ላይ መወያየትና መወሰን ይኾናል።
በዚሁም መሠረት በተጠቀሰው ዕለት ሠዓትና ቦታ እንድትገኙ የሰበካው መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባዔ  ለአባላት ጥሪ ያስተላልፋል።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Thursday 9 May 2013

የቀኝ ዐይን - ድንግል ማርያም

ሚያዝያ 28/2003ዓ.ም
በዲ/ን ብርሃኑ አድማስ
አፍጣኒተ ረድኤት ማርያም በጊዜ  ምንዳቤ ወአጸባ ለዐይን እምቀራንባ፤ አንቲ ውእቱ ረዳኢተ ያዕቆብ በቤተ ላባ፤ በኩሉ ኅሊናሃ ወበኩሉ አልባባ፤ዘኢታፈቅረኪ ነፍስ ትሠሮ እምሕዝባ፡፡

lidetaleMariam

የነገረ ማርያም ሊቅ(Marian Doctor)እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ እመቤታችንን በብዙ ምሳሌ እየመሰለ፣ እየተረጎመና እያመሰጠረ ብዙ ጊዜ አመስግኗታል፡፡ ምንም እንኳን እኛ የምናውቀው የምስጋና ድርሰቱ ለጸሎት የምንጠቀምበት ውዳሴ ማርያም ቢሆንም ከትርጓሜና ከስብከቶቹ ውጪ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ስንኝ ያላቸው የምስጋና ድርሰቶችን(Hymns) መድረሱን ታሪክ ጸሐፊው ሶዝመን መዝግቦልናል፡፡ ከነዚህ የምስጋና ድርሰቶቹ መካከልም ‹‹በእንተ ልደት››(On Nativity) እና ‹‹በእንተ ቤተ ክርስቲያን››(On the Church)በተባሉ ትልልቅ ድርሰቶቹም እመቤታችንን ደጋግሞ ያመሰግናታል፡፡

Friday 18 January 2013

ጥምቀት በቅዱስ ኤፍሬም




ጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም.
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ

ቅዱስ ኤፍሬም በጥምቀት ላይ እጅግ ጥልቅ የሆነ አስተምህሮ ያለው አባት ነው፡፡ ቅዱስ ኤፍሬም በጥምቀት የገሃነም እሳት ይጠፋል ይለናል፡፡ “የሰውነት ትኩሳት ከሰውነታችን በሚመነጨው ላቦት እንዲቀዘቅዝ እንዲሁ በጥምቀት የገሃነም እሳት ይጠፋል፡፡”

ጥምቀት


ጥር 9 ቀን 2005 ዓ.ም
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ

በሰው ልጅ ዘላለማዊ ድኅነት ውስጥ ትልቁን ድርሻ የሚይዘው ሥርዓተ ጥምቀት ከሌሎቹ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በቀዳሚነት የሚፈጸምና የማይደገም ሥርዓት ነው፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ “አንዲት ጥመቀት” በማለት የሥርዓተ ጥምቀትን አለመደገምና አለመሠለስ ገልጦ ተናግሯል /ኤፌ.4፥5/፡፡ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ተመዝግቦ እንደሚገኘውና፥ የታናሽ እስያ ክፍል በሆነችው ቁስጥንጥንያ በ381 ዓ.ም. የተሰበሰቡ 150 የሃይማኖት አባቶቻችን “ወነአምን በአሐቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኀጢአት፣ ለኀጢአት ማስተሥረያ /ኀጢአትን በምታስተሠርይ/ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን” በማለት የጥምቀትን አንድ መሆንና ኀጢአትን በደልን የምታርቅ፣ የምታስወግድ ስለመሆኗ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ተመርተው ተናግረዋል፡፡ ሃይማኖታቸውንም ገልጠዋል፡፡

Wednesday 9 January 2013