Friday 11 July 2014

የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክና ገድል


የቅዱስ ጴጥሮስ እና የቅዱስ ጳውሎስ ታሪክና ገድል


 
የቅዱሳን ሐዋርያት ታሪክ ገድልና ሥራ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ በሙሉ አልሰፈረም። አርባዕቱ ወንጌላት ሐዋርያት

እንዴት እንደተጠሩና እስከ ዕርገት ድረስ የነበራቸውን ሁኔታ ሲጽፉ፤ ወንጌላዊው ሉቃስ ደግሞ የሐዋርያትን ታሪክ እስከ

፷ዎቹ መጀመሪያ ያለውን ጽፏል።

ከዚህ በመለስ ያለውን የሐዋርያት ታሪክ ለማወቅ ግን ዋናው ምንጩ የቤተ ክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት ናቸው።

የሐዋርያት ደቀመዛሙርት እነ ፓፒያስ፣ ፖሊካርፐስ፣ አግናጥዮስ፣ ቀሌምንጦስ ዘሮም ወዘተ. የአባቶቻቸውን ታሪክ ጽፈው

አቆይተውልናል። በኋላ ጊዜም በ2ኛውና በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሱት የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ጸሐፍት እነ

አውሳብዮስ፣ ሩፊኖስ፣ ጄሮም ፣ ወዘተ. በትውፊት የተቀበሉትን መዝግበው አልፈዋል።

ቅዱሳን ሐዋርያት ገድላቸው የተጻፈላቸው፣ በዓላቸው የተከበረላቸው የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው። እኛም

ሐምሌ ፭ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን በታላቅ ድምቀት በዓላቸው ከሚከበረው ሐዋርያት መካከል የሐዋርያው የቅዱስ

ጴጥሮስና የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስን ታሪክ እንደሚከተለው አቅርበነዋል።