ጌታችን ወደዚህ ምድር መጥቶ የምስራቹን ቃል ሲያውጅ እስራኤላውያን የተቀበሉት በተደበላለቀ ስሜት ነበር፡፡ በአንድ በኩል ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ሲገዛ ስለነበር ከሮማውያን ቅኝ ግዛት ነጻ የሚያወጣቸው መሲህ ይፈልጋሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ለብዙ ዘመናት በባርነት ቀንበር ስለደከመ ተስፋ በመቁረጥ ተዳክሞ ነበር፡፡ መሲህ ቢመጣ እንኳ ይመጣል ብለው የሚጠብቁት ጦር ይዞ ሰራዊት አስከትሎ ነው ብለው ያምኑ ነበር፡፡ ስለዚህም ነው ክርስቶስን መሲህ ነኝ ብሎ ሲመጣ ለመቀበል ፈቃደኞች አልነበሩም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ጦር ሳይዝ ሰራዊት ሳያስከትል እንዲሁ ባዶ እጁን አርነት ላወጣችሁ መጥቻለሁ እያለ ደጋግሞ ተናግሯልና ነው፡፡ ምንም እንኳ አብዛኛው እስራኤላዊ የክርስቶስን መሲህነት ቢጠራጠርና ባይቀበለውም፣ በፍጹም እምነት እስከ መጨረሻው የተከተሉትም ነበሩ፡፡ ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነን ከፈሪሳውያን ወገን የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አይሁዳዊ ነው፡፡ቅድስት ቤተክርስቲያንም ይህን ታላቅ ሰው ለማዘከር የዐቢይን ጾም ሰባተኛ እሁድ በእርሱ ስም ሰይማ ታከብረዋለች ፡፡ ተከታዮቿ ምዕመናንም የእርሱን አሰረ ፍኖት እንዲከተሉ ትመክራለች ታስተምራለችም፡፡ ኒቆዲሞስ ማነው? |
በዊኒፔግ - ካናዳ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዜናዎች ብሎግ Blog of the Ethiopian Orthodox Tewahedo St Mary's and St Gabriel's Church in the City of Winnipeg, Manitoba, Canada
Wednesday, 28 March 2012
የክርስቲያን ፊደል- ኒቆዲሞስ
Tuesday, 27 March 2012
ጸሎት በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ መጋቢት 18/2004 ዓ.ም.

|
Saturday, 24 March 2012
Thursday, 22 March 2012
ገብርኄር
ገብርኄር |
መጋቢት 13/2004 ዓ.ም. በዲ/ን አባተ አስፋ ዛሬ ታላቁን የጌታችንን ጾም ከጀመርን ስድስተኛ ሳምንት ላይ ደርሰናል፡፡ ይህን ሳምንት ቅድስት ቤተክርስቲያን «ገብርኄር» የሚል ስያሜ ሰጥታዋለች፡፡ ገብርኄር በጎ አገልጋይ ማለት ሲሆን የስያሜውን መነሻ የምናገኘው በዕለቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ከሚነበበው የወንጌል ክፍል ማቴ.25-14-30 ነው፡፡ |
Wednesday, 21 March 2012
Debre Zeit 2012 celebration in Winnipeg, CANADA photos
ደብረ ዘይት 2004 በአል ፎቶዎች
Debre Zeit 2012 celebration at the Ethiopian Orthodox Debre Genet St Mary's and St Gabriels church in Winnipeg Canada photos
click here to view photos
Tuesday, 20 March 2012
Monday, 19 March 2012
Friday, 16 March 2012
የዐቢይ ጾም ስብክት (ክፍል 5)
የዐቢይ ጾም ስብክት (ክፍል 5) |
መጋቢት 7/2004 ዓ.ም. በአያሌው ዘኢየሱስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ የዐቢይ ጾም አምስተኛ ሳምንት ሰንበት «ደብረ ዘይት» ተብሎ ይጠራል፡፡ ደብረ ዘይት ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ተራራው በዚህ ስም የሚጠራው ለዘይት የሚሆን የወይራ ተክል በብዛት ስለሚበቅልበት ነው፡፡ ጌታችን ቀን ሲያስተምር ውሎ በደብረ ዘይት ያድር ነበር፡፡ ለደቀ መዛሙርቱም ለሕዝቡ በምሳሌ ያስተማረውን ይተረጉምላቸው ነበር፡፡ የዓለም ፍጻሜና የዳግም ምጽአቱን ምልክት ለደቀ መዛሙርቱ ያስተማራቸው በዚሁ ተራራ ላይ ነውና የጌታን ዳግም ምጽአት የምናስብበት አምስተኛው የዐቢይ ጾም ሰንበት ስሙን ከተራራው ወስዷል ማለት ነው፡፡ ደብረ ዘይት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ «እኩለ ጾም» ተብሎ ይጠራል፡፡ በዚህ ስያሜ የሚጠራውም የጾሙ ሳምንታት አጋማሽ ወይም እኩሌታ ስለሆነ ነው፡፡ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አባቶች መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዕለተ እሑድ፣ የደብረ ዘይት ዕለት ይመጣል ብለው ስለሚያስተምሩ በዚህ ሰንበት የሚበዙት ምዕመናን ዕለቱን በታላቅ ዝግጅት ማለትም በንስሓና በቅዱስ ቁርባን ይቀበሉታል፡፡ በዚህ ዕለት የሚሰበከው ምስባክ፣ የሚሰጠው የወንጌል ትምህርትና የሚነበቡት የሐዋርያት ሥራና የመልእክታት ንባባት በሙሉ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ሁለተኛ አመጣጥ የሚናገሩ ናቸው፡፡ |
Wednesday, 14 March 2012
Monday, 12 March 2012
"መውደቅ አዳማዊ ነው፤ ወድቆ አለመነሣት ግን ዲያብሎሳዊ ነው”
"መውደቅ አዳማዊ ነው፤ ወድቆ አለመነሣት ግን ዲያብሎሳዊ ነው" |
መጋቢት 3/2004 ዓ.ም. በዲ/ን ኅሩይ ባየ “ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ” ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቤተ ክርስቲያን ካፈራቻቸው መተርጉማን፣ ሰባኪያንና የእምነት አርበኞች መካከል አንዱ ነው፡፡ ከአሕዛብነት ወደ ክርስትና የተመለሱ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ክርስቲያን ተብለው በተጠሩበት የሦርያ ዋና ከተማ በሆነችው በአንጾኪያ ተወልዶ ያደገው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሕይወቱ በአርአያነቱ የሚጠቀስ መንፈሳዊ አባት ነው፡፡ |
Friday, 9 March 2012
Thursday, 8 March 2012
አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ
አርባ መአልትና አርባ ሌሊት ጾመ ማቴ.4፥2 |
የካቲት 29/2004 ዓ.ም. በመ/ር ምሥጢረሥላሴ ማናየ ይህ ከላይ ያነሣነው ርዕስ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችንና አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ መአልትና አርባ ሌሊት መጾሙን ያስተምረናል፡፡ በዚህ ኀይለ ቃል ሁለት ታላላቅ ቁም ነገሮችን ቃላትን እንመለከታለን |
Wednesday, 7 March 2012
በገና - ሊቀ መዘምራን ይልማ አዝላው ወረደች ወደ ግብጽ Begena - Liqe Mezemeran Yilema Hailu - Azlaw weredech
በገና - ሊቀ መዘምራን ይልማ
አዝላው ወረደች ወደ ግብጽ
Saturday, 3 March 2012
የዐቢይ ጾም ስብከት (ክፍል 3)
የዐቢይ ጾም ስብከት (ክፍል 3) |
የካቲት 24/2004 ዓ.ም. በአያሌው ዘኢየሱስ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፤ መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጥምቁ ዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ወንዝ በተጠመቀ በሦስተኛው ቀን በገሊላ አውራጃ በቃና መንደር ከእናቱ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ከአሥራ ሁለት ሐዋርያቱ ጋር በዶኪማስ ቤት ሠርግ ተጠርቶ ነበር፡፡ በዚያም ወይን ጠጅ አልቆባቸው አፍረውና ተሸማቀው የነበሩትን ጋባዦች ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ውኃውን የወይን ጠጅ አድርጎ በመቀየር ከዕፍረት አድኗቸዋል፤ ክብሩን በመጀመሪያ ተአምሩ ገልጧል፤ ደቀ መዛሙርቱም በእርሱ አምነዋል፤ዮሐ 2፥1-11፡፡ |
Subscribe to:
Posts (Atom)