በዊኒፔግ - ካናዳ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዜናዎች ብሎግ Blog of the Ethiopian Orthodox Tewahedo St Mary's and St Gabriel's Church in the City of Winnipeg, Manitoba, Canada
Monday, 30 April 2012
Thursday, 26 April 2012
Wednesday, 25 April 2012
Sunday, 22 April 2012
የትንሣኤው ትርጉም በዓሉና አከባበሩ
ከሊቀ ትጉሃን ኀ/ጊዮርጊስ ዳኘ
በጠ/ቤተ ክህነት የዕቅድና ልማት መምሪያ ምክ/ሓላፊ
- «ትንሣኤ» የሚለው ቃል የግእዝ ቋንቋ ነው፡፡
- መገኛ ቃሉም «ተንሥአ» = ተነሣ የሚለው ግሥ ይሆናል፡፡ - «ትንሣኤ» ማለት ታዲያ = መነሣት፣ አነሣሥ ሐዲስ ሕይወት ማግኘት ማለትን ያመለክታል፡፡ - «ትንሣኤ» በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በየመልኩ፣ በየዐይነቱ ሲተረጐም ዐምስት ክፍል አለው፡፡ |
Friday, 20 April 2012
Saturday, 14 April 2012
ትንሣኤ ዘክርስቶስ
፩፦ ትንሣኤ ዘክርስቶስ፤
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነተ ዓለምን በመስቀል ላይ ከፈጸመ በኋላ በአካለ ሥጋ ወደ መቃብር ወረደ÷ ይኸውም በመቃብር ፈርሶ በስብሶ መቅረትን ሊያስቀርልን ነው፡፡ በአካለ ነፍስ ደግሞ ወደ ሲኦል ወረደ÷ ይኸውም በሲኦል ለነበሩ ነፍሳት ነፃነትን ይሰብክላቸው ዘንድ ነው፡፡ መለኮት፥ በተዋሕዶ፥ ከሥጋም ከነፍስም ጋር ነበረ፡፡ ለዚህ ነው፥ መቃብር ሥጋን ሊያስቀረው ያልቻለው፤ ሲኦልም ነፍስን ማስቀረት አልተቻለውም፡፡ ቅዱስ ዳዊት፡- « ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተዋትም» ያለው ይኽንን ታላቅ ምሥጢር በትንቢት ቃል ሲናገር ነው፡፡ መዝ ፲፭÷፲፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም፡- «ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር (ወደ አብ÷ ወደ ራሱና ወደ መንፈስ ቅዱስ) እንዲያቀርበን፥ እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት (ስለ ሰው ልጆች ኃጢአት ተላልፎ በመሰጠት) ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ (በፈቃዱ ነፍሱን ከሥጋው ለየ)÷ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ÷ (ያን ሥጋ ነፍስ እንድተለየችው መለኰት አልተለየውም)÷ በእርሱም ደግሞ (መለኰት በተዋሐዳት ነፍስ) ሄዶ በወኅኒ ለነበሩት ነፍሳት ሰበከላቸው፤» ብሏል።
የትንሣኤ ትምሕርት በመ/ር ምሥጢረ ሥላሴ ማናየ
"ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን፤ በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን፤ አሰሮ ለሰይጣን፤ አግዐዞ ለአዳም፤ ሠላም እምይዕዜሰ፤ ኮነ፤ ፍስሐ ወሠላም፡፡" |
“ክርስቶስ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ዲያብሎስን አሰረው አዳምን ነጻ አወጣው ሠላም ከዛሬ ጀምሮ ሰላም ሆነ” ይህ ቃል የትንሣኤው የምሥራች ለምእመናን የሚታወቅበት ነው የሚቀድስ ካህን፣ ሰባኪ በዘመነ ትንሣኤ ከስብከቱ አስቀድሞ በዚህ ቃል የክርስቶስን መነሣት ያውጃል፡፡ የሚቀድሰው ካህንም በኪዳን ጊዜ ህዝቡን ከመባረኩ አስቀድሞ ይህንኑ ቃል ይናገራል ሰላምታ የሚቀባበሉ ምእመናንም ሰላምታ ከመስጠት አስቀድሞ ይህን ቃል በመናገር የትንሣኤውን አዋጅ ማወጅና መመስከር ይገባቸዋል፡፡ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰን አደረሳችሁ!!! |
Friday, 13 April 2012
Thursday, 12 April 2012
Wednesday, 11 April 2012
ጸሎተ ሐሙስ
ጸሎተ ሐሙስ |
በሊቀ ጠበብት ሐረገወይን አገዘ ጸሎተ ሐሙስ ነቢያት በሀብተ ትንቢት በመንፈሰ ትንቢት ‹‹እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት›› /መዝ. 117፥24/ በማለት ትንቢት የተናገሩላት በቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ትላልቅ የተባሉ ምሥጢራት የተፈጸሙባት ዕለት ናት፡፡ |
Sunday, 8 April 2012
ሥርዐተ ሰሙነ ሕማማት
ሥርዐተ ሰሙነ ሕማማት
(ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002 ::
ስንክሳር- የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ )
ሥርዐት ምንድን ነው?
“ወንድሞች ሆይ፡ ከእኛ እንደተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሔድ
ወንድም ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
…በእናንተ ዘንድ ያለሥርዐት አልሔድንምና። “ (2ኛ ተሰ. 3፡ 6)
ወንድም ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን።
…በእናንተ ዘንድ ያለሥርዐት አልሔድንምና። “ (2ኛ ተሰ. 3፡ 6)
ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ ክንዋኔዎች በሰሙነ ሕማማት
(ምንጭ፦ ስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት መጋቢት 2002 ::
ስንክሳር- የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ )
በዐቢይ ጾም ከሠርክ ሆሣዕና ጀምሮ እስከ ትንሣኤ ሌሊት
ዕለታት የሚገኙበት ሳምንታት ሰሙነ ሕማማት ይባላሉ፡፡
ዕለታቱም የዓመተ ፍዳ፣ የዓመተ ኩነኔ መታሰቢያ ናቸው፡፡
በእነዚህ ዕለታት ውስጥ የተለያዩ ትውፊታዊ እና ሃይማኖታዊ
ክንዋኔዎች አሉ፡፡ ከነዚህ ክንዋኔዎች ውስጥ አለመሳሳም፣
አክፍሎት፣ቄጤማ ማሰር፣ ጥብጣብ፣ ጉልባን እና
ሕጽበተ እግር ይገኙበታል፡፡
Wednesday, 4 April 2012
Monday, 2 April 2012
Sunday, 1 April 2012
Subscribe to:
Posts (Atom)