ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
"ትኩስ ወይም በራድ ስላልኾንኽ ልተፋህ ነው"
ክፍል አንድ
"ትኩስ ወይም በራድ ስላልኾንኽ ልተፋህ ነው"
ክፍል አንድ
በዊኒፔግ - ካናዳ - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ወቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ዜናዎች ብሎግ Blog of the Ethiopian Orthodox Tewahedo St Mary's and St Gabriel's Church in the City of Winnipeg, Manitoba, Canada
| ዘመነ ጽጌ |
ከገነት የተሰደደውን አዳምን ወደ ቀደመ ክብሩና መንበሩ ከዚያም ወደ ሚበልጥ ክብር ለመመለስ የተወለደው ጌታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገና ከህፃንንቱ ጀምሮ ስደትን እና መከራን ተቀብሏል፡፡ ጌታ ሲወለድ ሰብአ ሰገል «የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት አለ? በምሥራቅ ኮከቡን አይተን ልንስግድለት መጥተናል» እያሉ በኮከብ እየተመሩ በመጡ ጊዜ በይሁዳ፣ በገሊላና በሰማርያ የሮማውያን ተወካይ የነበረው ንጉሥ ሄሮድስ የጌታችን ንግሥና ምድራዊ ንግሥና መስሎት መንግስቴን ሊቀማኝ ነው ብሎ ደነገጠ፡፡ ፊሪሳውያን «መሲህ ተወልዶ ከሮማውያን አገዛዝ ነጻ ያወጣናል፡፡» ብለው ያምኑ እንደነበር ስለሚያውቅም ይህ የተፈጸመ መስሎት ጭንቀቱ በረታ፡፡ የተወለደውን ሕፃንም ለመግደል ተነሳ፡፡ ስለዚህም ሰብአ ሰገልን አስጠርቶ «ሂዱ ሕፃኑን ፈልጉ ፤ ባገኛችሁትም ጊዜ እኔም እንድሰግድለት ወደ እኔ ተመልሳችሁ ያለበትን ንገሩኝ» በማለት በሽንገላ ተናገራቸው፡፡ |