ምሥጢረ ሥላሴ
እንኳን ለጥር ሥላሴ በዓል
በሰላም አደረሳችሁ!!
ምሥጢር
አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር ፣ ድብቅ ፣
ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱአዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር
የተባሉበት ምክንያት
- በሥጋዊ ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
- ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ
ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
የፈጣሪ ምሥጢር፡- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡ ከ እስከ የሌለው ምሥጢርም
ይባላል፡፡
የፍጡራን ምሥጢር፡- በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅ/ ነው፡፡
የሰውና የመላእክትምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡
ምሥጢረ ሥላሴ
ሥላሴ፡- የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን
ሦስት ፣ሦስት ሲሆን አንድ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሦስትነት ልዩ ሦስት ነው፡፡
ሦስት ብቻተብሎ አይቆምምና ሦስት ሲሆን አንድም ነው፡፡
ስለዚህ እግዚአብሔር የአንድነትየሦስትነት ባለቤት በመሆኑ ሥላሴ ይባላል፡፡
የእግዚአብሔር አንድነት
እግዚአብሔር አንድ ነው ስንል በመለኮት ፣ በባሕርይ ፣ በአገዛዝ ፣
በሥልጣን ፣ በሕላዌ/ሕልውና/ በመፍጠር በልብ በቃል በእስትንፋስ
ይህን ዓለም በመፍጠር እና በማሳለፍይህን በመሳሰለው ነው፡፡
በመፍጠር መዝ 101፡25 ፣ ዘፍ 1፡1 ፣ ኢሳ 66፡1-2
በሥልጣን ዮሐ 10፡30
በመለኮት መለኮት ማልኩት ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን
መንግስት ግዛትማለት ነው፡፡ ይህም ለእግዚአብሔር ብቻ የተሰጠ ነው፡፡
ቆላ 2፡9፣ 1ኛ ጴጥ 1፡3
በሕላዌ /ሕልውና/ አኗኗር ማለት ነው፡፡ መብለጥ ፣
መቅደም ፣ መቀዳደምየለባቸውም፡፡ ዮሐ 1፡1-2፣ ዮሐ 14፡10
የእግዚአብሔር ልዩ ሦስትነት
እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ነው፡፡
የስም ሦስትነት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ናቸው፡፡ ማቴ 28፡19፡፡
እግዚአብሔር አብ፡- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት
የአንዱ የአብ ስም ነው፡፡1ኛ ጴጥ 1፡2፣ ዮሐ 3፡16
እግዚአብሔር ወልድ፡- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት
የአንዱ የወልድ ስምነው፡፡ ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ በተለያ ስሞች ተጠርቷል፡፡
እነዚህም፡-
ኢየሱስ- መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው፡፡ ማቴ 1፡21
ክርስቶስ- መሲሕ /ንጉሥ/ ማለት ነው፡፡ ሉቃ 2፡11፣ ዮሐ 4፡25
አማኑኤል-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው፡፡
ትን.ኢሳ 7፡14 ፣ ማቴ1፡21
እግዚአብሔር ወልድን አምላክነት አስረጂ
የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ዮሐ 20፡9 ፣ ሮሜ 10፡12 ፣ ዮሐ 1፡1 ፣ ዮሐ 1፡14 ፣
ዮሐ 20፡28 ፣ ዮሐ4፡42 ፣ የሐዋ.ሥራ 20፡28 ፣ ራዕይ 1፡8 ፣
ትን.ኢሳ 9፡6 ፣ ራዕይ 22፡12 ፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ከሦስቱ አካላት
የአንዱ መንፈስ ቅዱስ ስሙ ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡
- መንፈስ- ዮሐ 3፡5 ፣ 1ኛ ቆሮ 12፡4 ፣ ዘፍ 1፡2 ፣ ትን.ኢሳ 48፡16
- የእግዚአብሔር መንፈስ - ት.ኢሳ 61፡6
- ጰራቅሊጦስ /አጽናኝ/ እየተባለ ይጠራል፡፡ ዮሐ 15፡26 ፣ ዮሐ 14፡16 ፣ ዮሐ16፡7
- የእውነት መንፈስ፡፡ ዮሐ 15፡26
የአካል ሦስትነት
ለአብ ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አለው፡፡
ለወልድም ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አለው፡፡
ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም ገጽ ፣ ፍጹም መልክ ፣ ፍጹም አካል አለው፡፡
የግብር ሦስትነት
የአብ ግብሩ መውለድ ማስረጽ ፣ የወልድ ግብሩ መወለድ ፣ የመንፈስ ቅዱስ ግብሩመስረጽ ነው፡፡ አብ ወልድን ውልዷል ፤ መንፈስ ቅዱስን አስርጽዋል ፤ መንፈስ ቅዱስከአብ ሰርጽዋል፡፡ ወልድ ከአብ ተወልዷል ፡፡
- አብ ወልድን ወለደ ማለት ፤ ከአካሉ ከባሕርይው ፤ አስገኘው ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የሰው ነፍስ ልብነቷ /አሳቢነቷ/ ቃልነቷን እንደሚያስገኘው
- ወልድ ከአብ ተወለደ ማለት ፤ አብን አክሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለትነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ቃልነቷ ከልብ እንደተገኘ
- አብ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸው ማለት ፤ ከአካሉ ከባሕርይው አስገኘው ማለትነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ልብነቷ እስትንፋስነት /ሕይወትነቷን/ እንዳስገኘ ማለት ነው
- መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸማለት ፤ አብን አህሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለትነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ እስትንፋስነቷ ከልብ እንደተገኘ
ለምሥጢረ ሥላሴ የፍጡራን ምሳሌ
የሰው ነፍስ፡- የመናገር ፣ የማሰብ ፣የመተንፈስ /የሕያውነት/ ሁኔታ አላት፡፡
ማሰብ በአብ ፤ መናገር በወልድ ፤ ሕያውነት በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡
የነፍስ ልብነቷ ቃልነቷን ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለች፡፡
ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች እንጂ ልብነቷ ቀድሞ
ቃልነቷ እስትንፋስነቷበኋላ አልተገኘም፡፡ ነፍስ በኩነታት ሦስትነት
ቢኖራትም በአካል አንድ ናት፤ ሥላሴ ግንአብ አካላዊ ልብ፤
ወልድ አካላዊ ቃል ፤ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡
ፀሐይ፡- አንድ ስትሆን ሦስትነት አላት፡፡ አካሏ ፣ ብርሃኗ ፣
ሙቀቷ ናቸው፡፡ አካሏበአብ፣ ብርሃኗ በወልድ፣ ሙቀቷ
በመንፈስ ቅዱስ ይመስላል፡፡
ባሕር፡- ስፋቱ በአብ፣ ርጥበቱ በወልድ ፣
ማዕበሉ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡
ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የማገናዘቢያ ጥቅሶች ፡-
በብሉይ ኪዳን
ት.ኢሳ 48፡12 ፣ መዝ 117፡16፣ ዘኁ 6፡24 ፣
ዘፍ 3፡22 ፣ት.ኢሳ 6፡3
በሐዲስ ኪዳን
1ኛ ቆሮ 19፡14 ፣ ማቴ 17፡15 ፣ ሉቃ3፡22 ፣ ማቴ 28፡19 ፣
ማቴ 3፡16 ፣ ዩሐ16፡7 ፣ የሐዋ.ሥራ 7፡55 ፣ ዮሐ 14፡15 ፣ ራዕይ 14፡1-2
በዓሉን በዓለ ሰላም ፤ በዓለ ክብር ፤ በዓለ ፍስሐ ያድርግልን - አሜን!!
No comments:
Post a Comment