Wednesday, 26 September 2012

ቅዱስ መስቀል ፍቅር ነው

መስከረም 15 ቀን 2005 ዓ.ም.
አባ ዘሚካኤል

meskele 1ወሶበ ርእዮሙ እግዚእ ኢየሱስ ለእሙ ወለረድኡ ዘያፈቅር ይቀውሙ፤ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደውን ደቀ መዝሙርና እመቤታችንን ከእግረ መስቀል ቁመው ባያቸው ጊዜ፣ ወይቤላ ለእሙ ኦ ብእሲቶ ነዋ ወልድኪ፤ አንቺ ሆይ ልጅሽ ይርዳሽ ያጽናናሽ አላት፡፡ ውሉድኪ ሲል ነው በዮሐንስ እኛን ለርስዋ መስጠቱ ነውና፡፡ ወይቤሎ ለውእቱኒ ረድ ነያ እምከ፣ ደቀ መዝሙሩንም እነኋት እናትህ ታጽናህ አለው እምክሙ ሲል ነው፡፡ በዮሐንስ እርስዋን ለኛ መስጠቱ ነውና፡፡(ዮሐ. 19: 26-27)

Monday, 24 September 2012

መስቀሉ የት ነው ያለው?

ከዳንኤል ክብረት

(ምንጭ- ስንክሳር- የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ)



በእምነትታሪክ ውስጥ የታሪክ፣የአርኬዎሎጂ እናየቅርስ ጥናት ሰዎችንያስጨነቁ ሁለትጥያቄዎች አሉ፡፡ ታቦተጽዮን እና ጌታየተሰቀለበት መስቀልየት ነው ያሉት?የሚሉት ጥያቄዎች፡፡እነዚህን ጥያቄዎች ለመመለስ አሰሳዎች፣ ቁፋሮዎች፣ መዛግብትን የማመሳከር ሥራዎች፣ አሉ የተባሉየይዞታ ጥያቄዎችን የመመርመር ፍተሻዎች በመካሄድ ላይ ናቸው፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ግን የዓለም ቅርሶች መናኸርያ የሆነችው ኢትዮጵያ ሁለቱንም በተመለከተ ለዓለም የምትገልጣቸው ነገሮች አሏት፡፡

Saturday, 15 September 2012

መስቀልና እመቤታችን


በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ (ምንጭ፡ ደቂቀ ናቡቴ ብሎግ)
  • መግቢያ 
በአንድ ቤተሰብ ውስጥ ለእያንዳንዱ የቤተሰብእ አባል የራሱ የሆነ ቦታ ወይም ደረጃ አለው፡፡ እናት ያላት ቦታ አለ፡፡ አባት ያለው ቦታ አለ፡፡ ልጆች ያላቸው ቦታ ደግሞ ይኖራል፡፡ የልጆች ቦታ እንኳን እንደ እድሜያቸውም ሆነ እንዳላቸው የትምህርት፣ የሥራና የሥነ ምግባር ሕይወት የተለያየ ነው፡፡ የታላቅ ልጅ ቦታ ከታናሽ ይለያል፡፡
ይህ ዓይነቱ የመዋቅር ልዩነት በየትም ቦታ ይታያል፡፡ በወታደር ቤት ይህ ልዩነት አለ፡፡ በቢሮና በማናቸውም መድረክ ይህ ዓይነቱ ልዩነት የተጠበቀ ነው፡፡ ሌላው ቀርቶ በአንድ ሰው ውስጥም በአካል ብልቶች መካከል ይህ ልዩነት አለ፡፡ ልዩነቱ የኃላፊነት፣ የወሳኝነትና የአስፈላጊነት መጠንን ይገልጣል፡፡ ይህን ልዩነት ተከትሎ የሚመጣ ነገር ደግሞ አለ፡፡ ይኸውም የክብር ልዩነት ነው፡፡

Monday, 10 September 2012

“አዲስ ልብና አዲስ መንፈስ ለእናንተ አድርጉ” /ሕዝ 18፥31/


በማሞ አየነው
የሰው ልጅ ለሥጋዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴው አመች በሆነ መልኩ እግዚአብሔር ለሚያፈራርቃቸው ዘመናት ቀመር ሲያወጣ ኖሯል፡፡ ጊዜያትንም ከደቂቃ ሽራፊ እስከ ሺህ ዘመናት ድረስ ከፋፍሎ ይጠቀማል፡፡ በዚህ የጊዜ ቀመርም ትናንትን ያስረጃል፤ ዛሬን ደግሞ አዲስ ያደርጋል፡፡ በጊዜ ዑደትም ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት አልፈው ብዙ ሺህ አዲስ ዓመታት መጥተዋል፡፡ የዘመናት መፈራረቅ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ እንዲያደንቅ፣ መግቦቱንም እንዳይረሳ ያደርጋል፡፡ እግዚአብሔር አምላክም ቃል ኪዳኑን እንዳልረሳ፣ ፍጥረቱን እንዳልዘነጋ ያመለክታል፡፡

ዘመነ ማቴዎስ ወንጌላዊ እና ቅዱስ ድሜጥሮስ ተካሌ ወይን


በ

ማቴዎስ ወንጌላዊ
እንኳን ለዘመነ ማቴዎስ 2005 ዓ.ም. በሰላም አደረሳችሁ  
ዕንቁጣጣሽ
አዲሱ ዓመት የንስሐ ፤ የቅድስና ፤ የደስታ ፤ የፍስሐ ፤ የፍቅር ያድርግልን


ድሜጥሮስ መስታወት ነው፡-በመስታወት ከዓይን ጉድፍ ከጥርስ እድፍ አይተው እንደሚያጸዱበት ሁሉ ባሕረ ሐሳብንም የተማረ ሰው ዓለም ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ እስከ ምጽአት ድረስ የሚሆነውን ቁጥር ያውቃልና፡፡ ባሕረ ሐሳብ ማለት ቁጥር ያለው ዘመን ማለት ነው፡፡ አንድም ሐሳብ ባሕር ይለዋል ዘመን ያለው ቁጥር ሲል ነው፡፡

Friday, 17 August 2012

ምሥጢረ ደብረታቦር


አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ  ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ
ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ ፤ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንምለኤልያስ እንሥራ  ›      
 ቅዱስ ጴጥሮስ

ታቦር ተራራ የዛሬ ገጽታው
           ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ቅዱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሌያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ከኤልያስ እንሥራ አለ።

Wednesday, 8 August 2012

ጾመ ፍልሰታ


ነሐሴ 1 ቀን 2004 ዓ.ም.
በዲ/ን ዮሴፍ ይኲኖ አምላክ
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡ ፈጣሪያችን ጾሙን የበረከት፣ የረድኤት የንስሓ ያደርግልን ዘንድ ቅዱስ ፈቃዱ ይሁንልን፡፡ ንስሓ ገብተን፣ ጾመን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን ሕይወት እንድናገኝ የፈጣሪያችን ቸርነቱ አይለየን! አሜን

ጾም፡- መተውን መከልከልን መታቀብን፣ መታረምን የሚገልጥ የግብር ስም ነው፡፡

kidaseየቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓትና የሕግ መጽሐፍ የሆነው ፍትሐ ነገሥት በ15ኛው አንቀጹ መግቢያ ላይ “ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው፡፡ በደሉን ለማስተሥረይ ዋጋውን ለማብዛት እርሱን ወዶ ሕጉን ለሠራለት እየተታዘዘ የፈቲዉን ኀይል ያደክምበት ዘንድ ለነባቢትም ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ፤” በማለት የጾምን ምንነትና ጥቅም አጠር አድርጎ ያብራራል፡፡

Tuesday, 7 August 2012

ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር


እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ
















ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪመካነ ፍሥሐ ምጡቀ ፤ በአእባነ ባህርይ ዘተነድቀ ፤ ማርያም ደብተራ እንተ ኢትትከደኒ ሠቀ

እመቤቴ ማርያም ሆይ ምጡቅና ሩቅ ወደሚሆን የደስታ ቦታ ላረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል ፡፡ ይኸውም ኅብሩ ሊመረምሩት በማይቻል ዕንቊ የታነፀ ሕንፃ ይገኝበታል፡፡
               መልክአ ማርያም