Friday 28 December 2012

ታኅሣሥ ገብርኤል


ዲያቆን መልአኩ እዘዘው

ገብርኤል ማለት “እግዚእወገብር” -የእግአብሔር አገልጋይ ማለትነው። ፍጥረታት መፈጠር በጀመሩበትበዕለተ እሑድ እግዚአብሔር መላእክትን ከፈጠራቸው በኋላ ተሰወራቸው መላእክትም “መኑ ፈጠረነ፡ ማንፈጠረን” ሲሉ ዲያብሎስ እኔፈጠርኳችሁ ብሎ መላእክት በተረበሹጊዜ “የፈጠረንን አምላካችን እስክናውቅበያለንበት ጸንተን እንቁም”  ብሎያረጋጋቸው መልአክ ነው። በዚህምምክንያት ጌታ “በእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም” እንዲልሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስርአድሎታል። ከዚህም በኋላ ደጋግሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድሆኗል።ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ በተረዳኢነቱና በአማላጅነቱ በክርስቲያኖች ዘንድ ይወደዳል፡፡ ምክንያቱም ያዘኑትን ለማጽናናት የምሥራች ለመንገር ከእግዚአብሔር ወደ ምእመናን ይላካልና፡፡
በዚህም ዕለት በታህሳስ 19 እግዚአብሔር አገልጋይ የሆኑትን አናንያ አዛርያ ሚሳኤልንከእቶነ እሳት አድኗቸዋል። (ትንቢተ ዳንኤል ዕራፍ 3)
ነገሩ እንደዚህ ነው -
አናንያ አዛርያ ሚሳኤልን ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ሲኖሩ ንጉሡ ናቡከደነጾር ዳንኤልንአራተኛ አድርጎ ጥበበ ባቢሎን ይማሩ ብሎ ከቤተ - መንግሥት  አስቀመጣቸው።መጋቢያቸው ሜልዳር ሥጋ በገበታ ጠጅ በዋንጫ አቀረበላቸው። “ይህንን አንበላምጥቂት ጥሬ እና ጥሩ ውኃ ስጠን” አሉት። “ንጉሥ ከስታችሁ ቢያይ ይቆጣል” አላቸው።ቀን ስጠን” ቢሉት 10 ቀን ሰጣቸው። ጥሬ እየቆረጠሙ ውኃ እየጠጡ ሰንብተው ጮማከሚበሉት ጠጅ ከሚጠጡት ይልቅ አምረው ደምቀው ተገኙ። 
በዚሁ ሲማሩ ቆይተው ጌታ ጥበቡን ገልጾላቸው ጠቢባን ሲሆኑ ይልቁንም ዳንኤልርእሱ ዘወርቅን ለንጉሱ ከተረጎመለት በኋላ በሦስት አውራጃዎች ሾማቸው።ባቢሎናውያን ቀንተው ለማጣላት ምክንያት ይሆነናል ብለው “ንጉሥ እንዳየኸው ምስልአድርገህ አሰርተህ አቁም ወዳጅ ጠላትህን በሱ ትለያለህ” አሉት። 70  ክንድቁመት፣ 6 ክንድ ስፋት ያለው የወርቅ ምስል አሰርቶ በአዱራን ሜዳ አቁሞ “ያልሰገደይቀጣል” ብሎ አዋጅ ነገረ። ሁሉ ሲሰግዱ ሠለስቱ ደቂቅ “አንሰግድም” አሉ። ሄደውነገሩት። አስጠርቶ “አንሰግድም አላችሁን?” አላቸው። “አዎን” አሉት። “መኑያድኅነክሙ እምእዴየ፤ ማን ያድናችኋል?” አላቸው። “ሀሎነ አምላክነ ዘፈጠረ ኪያከወኪያነ፤ እኛንና አንተን የፈጠረ አምላካችን ያድነናል” አሉት። ነበልባሉ 49 ክንድ የሆነእሳት አስነደደ።
ከዚህ በኋላ ኃያላኑን መርጦ የኋሊት አሳስሮ ከእሳቱ አስጣላቸው። እኒያን ወላፈኑገድሏቸዋል። እነርሱን ግን “ወወረደ መልአከ እግዚአብሔር ምስለ እለ አዛርያ ውስተእቶን ወዘበጦ ለነበልባለ እሳት ወረሰዮ ከመ ማይ ቆሪር ዘጊዜ.ጽባሕ” ይላል ቅዱስገብርኤል ወርዶ በዘንጉ ቢነካው ውኃ ሆኗል። ባቢሎናውያን የቀደመው  ሲጠፋጨማምረው አነደዱባቸው። 

እነርሱ ግን ምንም ሳይሆኑ ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ፤ ስቡህኒ ውእቱወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም። እያሉ ሲያመሰግኑ አድረዋል።
በጧት ናቡከደነጾር ከሰገነቱ ሆኖ ሲመለከት አራት ሆነው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱአይቶ  ትናንት ሦስት ሰዎች አስረን ከእሳቱ እቶን ጥለን ነበር፤  ዛሬ ግን አራት ሆነውከእሥራታቸው ተፈትተው በእሳቱ ውስጥ ሲመላለሱ አያለሁ።  እንደውምአራተኛው የእግዚአብሔር ልጅ ይመስላል” አለ።ወዲያውም ከእቶኑ ሔዶ “አንትሙሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብደናጎ አግብርተ.እግዚአብሔር ንዑ ፃዑ ዝየ፤ እናንተ ሲድራቅሚሳቅና አብደናጎ የእግዚአብሔር አገልጋዮች  ውጡ።” አላቸው። ምንም ሳይሆኑወጥተዋል።በልብሳቸው ላይ ጥላት እንኳን አልተገኘም።
ናቡከደነጾር ይህን አይቶ “ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ ሲድራቅ ወሚሳቅ ወአብደናጎዘፈነወ መልአኮ ወአድኀነ አግብርቲሁ፤ መልአኩን ልኮ ባለሟሎቹን ያዳነ የሲድራቅየሚሳቅ የአብደናጎ አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።” አለ። “ንጉሥ እውነት መሰለህበሥራያቸው ነው” አሉት ባቢሎናውያኑ። “በሥራይ ከሆነማ ከእናንተ የሚበልጥ የለምበሥራያችሁ ዳኑ” ብሎ ከእሳቱ ጨምሯቸው ተቃጥለዋል። ንጉሡም “ከሲድራቅከሚሳቅ ከአብደናጎ አምላክ ከእግዚአብሔር በቀር ማዳን የሚቻለው የለምና እሱንአምላኩ ብሎ አዋጁን በአዋጅ መልሶታል። እነሱንም በሹመት ላይ ሹመት በክብር ላይክብር ጨምሮላቸዋል። (.ዳን .3)
የነደደ እሳት ውስጥ ገብቶ ከመውጣት ባልተናነሰ መከራ ውስጥ ገብተው በቅዱስገብርኤል አማላጅነት ከሞተ ሥጋ ነፍስ ድነው እውነተኛ ምሥክርነታቸውንየሚሰጡ ብዙዎች ናቸው፡፡ በመልአኩ ሥም በፈለቀው ጠበል ተጠምቀው ደዌየራቀላቸው እጅግ በርካታ ናቸው፡፡ በየዓመቱ በቁልቢና በሌሎች በቅዱስገብርኤል ስም በታነጹ አብያተ ክርስቲያናት የሚሰበሰበው ምዕመናን ሥዕለቱየሰመረለት ልመናው የተሰማለት እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ለመላእክትአለቃ ለቅዱስ ገብርኤል የተሰጠውን ጸጋ ተረድተን የመልአኩን አማላጅነትበመጠቀም ልናከብረው  ይገባል፡፡


የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል ጠባቂነቱ፣
 በሁላችን ላይ ለዘለዓለም ይኑር።
 አሜን።

No comments:

Post a Comment