Saturday 31 December 2011

Happy New Year!!

"And I said to the man who stood at the gate of the year, ‘Give me a light that I may tread safely into the unknown’. And he replied: “Go out into the darkness and put your hand into the hand of God. That shall be to you better than light and safer than a known way."

— From a poem entitled ‘God Knows’ written by Miss Minnie Louise Haskins in Bristol, England in 1908, revived by King George 6th in a broadcast he made during the darkest days of World War 2.

Wednesday 28 December 2011

በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል


በዓለ ክብሩ ለሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል
ታኅሣሥ 18/2004 ዓ.ም
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ
St.Gebrieale 1
ነቢዩ ዳንኤል “ዐይኖቼንም  አነሣሁ” አለና አስከትሎ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡… ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ  ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡(ዳን.10፡5-9)

ቅዱስ ገብርኤል - (የዲያቆን መልአኩ እዘዘው ገጽ)


                               ቅዱስ ገብርኤል


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል በዓል በሰላም አደረሳችሁ

















ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱና በእግዚአብሔር ፊት የሚቆመው ታማኝ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ 

Tuesday 27 December 2011

40th Day Memorial Service of Z/T Alem Zegeye



40th Day Memorial Service was held for our beloved sister Zemarit Alem Zegeye at her Debregenet St Mary's and St Gabriel's Church in Winnipeg, Canada on Sunday December 25, 2011. After the prayer service (Tselote Fethat)  a Wereb celebrating the joining of our blessed sister  with the saints in Heaven was presented by the choir. Food and refreshment  (Tsebel Tsedik) prepared by the church choir was also served to the hundreds of guests.

Here is the first part of the Wereb  - Wetequebelwa Melaikti Le Mahdere Maryam be Sibhat, which means the angels welcomed Mahdere Maryam with joy (Mahdere Maryam is Alem's baptismal name - Sime Kristina). Please also watch the second part.




40th Day Memorial Service of Z/T Alem Zegeye 2

Here is the second part of the Wereb  - Wetequebelwa Melaikti Le Mahdere Maryam be sibhat , which means the angels welcomed Mahdere Maryam with joy(Mahdere Maryam is Alem's baptismal name -Sime Kristina). Please also watch the first part if you have not done so.

Click here to watch part one

Saturday 24 December 2011

ነጠላ

ነጠላ
                                 (በሰሎሞን ሞገስ - ኮፌዳ ብሎግ)

    ሁሉን በጥበቡ ያደረገ እና ዓለሙ ሁሉ የእርሱ የሆነ እግዚአብሔር ሰዎች እንደአቅማቸው እና እንዲያስፈለጋቸው እንዲረዱት ባደረገው እና በሚያደርገው ሥነ ፍጥረት ሁሉ ሲታወቅ እና ሲመሰገን ይኖራል። ከዓለም እና ለዓለም ያይደሉ፣ በዓለም መሆናቸው ዓለሙን ወደተፈጠረበት ዓላማ መመለስ የሆነ ለአምላካቸው የተለዩ ክርስቲያኖችም፡- እርሱ እንዳስተማራቸው ለእግዚአብሔር ለሚያደርጉት የተለየ አገልግሎት ከራሳቸው ጀምሮ ሁሉን ይለያሉ ለዚህም ነው ቤተክርስቲያን ዘመናቱን በወንጌላውያኗ ሠይማ እና ቀድሳ፥፣ዓመቱን/፫፻፷፭ /፬ቱን/ሁሉ በምድር ያለች ሰማይ ሆና መንፈሳዊ ሒደቱን በመልክ በመልኩ ለእግዚአብሔር ስትለይ መጽሐፍቱን ፣አልባሳቱን፣ ዜማውን ከነመሣሪያዎቹ፣ ..........ንዋያቱን ሁሉም እንዲሁ ለአገልግሎቷ በመለየት የሆነው።

Friday 23 December 2011

የምእመናን መሰባሰብ፤ የቅዳሴ ቀዳሚ ምስጢር


የምእመናን መሰባሰብ፤ የቅዳሴ ቀዳሚ ምስጢር

ታኅሣሥ 13/2004 ዓ.ም
በዲ/ን በረከት አዝመራው

ቅዳሴ የአንዲቷ ሰማያዊት ቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ገጽ እንደሆነ ሁሉ የምእመናን መሰባሰብ ደግሞ የቅዳሴ የመጀመሪያ መሠረት ነው፡፡ kidaseበመሰባሰብ የፈጸመው የቅዳሴ ሥርዓታችን አስቀድሞም በቅዱሳን መላእክት ዓለም የነበረና በምድር ባለች መቅደሱም በምእመናን መሰባሰብ የሚፈጸም ነው፡፡ “እኔ በመካከላቸው እሆናለሁ” ብሎ ደስ የሚያሰኝ ዘላለማዊ ቃል ኪዳን የገባልን ጌታችን፣ “ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት” በማለት መሰባሰባችን ጸጋና ረድኤቱን እንድናገኝ ምክንያት መሆኑን ነግሮናል /ማቴ.18፥20/ በዚህ ርዕስም የጌታን ቃል በታላቅ ትጋት በፈጸመች ሰማያዊ ሥርዓቷን ከቅዱሳን መላእክት ዓለም ያገኘች፣ የምስጋና ሥርዓቷም በትውፊት ደርሶ ለቤተ ክርስቲየን መሠረት በሆነው በጠንታዊት /በሐዋርያት ዘመን/ ቤተ ክርስቲያን ለምእመናን መሰባሰብ ይሰጥ የነበረውን ትኩረትና ምስጢራዊ እይታ እንመለከታለን፡፡

Wednesday 14 December 2011

Tuesday 13 December 2011

በአታ ለማርያም


በአታ ለማርያም

ታኅሣሥ 3/2004 ዓ.ም
በዲ/ን ሽመልስ መርጊያ

Mariam1ሰይጣን በእባብ አካል ተሰውሮ ሔዋንን፤ በእርሱዋም አዳምን በማሳት በእነርሱ ላይ ሞት እንዲሠለጥንባቸው ስላደረገ “በአንተና በሴቲቱ መካከል፣ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደረጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኮናውን ትነድፋለህ” በማለት የፍቅር አምላክ እግዚአብሔር ፈረደበት፡፡ “በአንተ” የተባለው ሰይጣን ሲሆን፣ “በሴቲቱ” የተባለችው ቅድስት ድንግል ማርያም ናት (ገላ.4፡4)፣ “በዘርህ” ሲል የዲያብሎስ የግብር ልጆችን ሲሆን(ዮሐ.8፡49)፣ “በዘርዋ” የተባለው ክርስቶስ ነው(ገላ.3፡16)፡፡ ትርጉሙ እንዲህ አንደሆነም ወንጌላዊው ዮሐንስ “ዘንዶው በሴቲቱ ላይ ተቆጥቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የጠበቁትን የኢየሱስም ምስክር ያላቸውን ከዘርዋ የቀሩትን ሊዋጋ ሄደ በባሕርም አሸዋ ላይ ቆመ”አለን፡፡(ራእ.12፡17) እባብ የተባለው ሰይጣን ስለመሆኑም “ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ”(ራእ.12፡9) ብሎ ጻፈልን፡፡

Saturday 10 December 2011

በዊኒፔግ ካናዳ የ2004 ኅዳር ጽዮን በዓል ፎቶዎች Hidar Tsion 2011 Festival in Winnipeg, CANADA - photos

‎"ጽዮንን ክበቡአት፥ 
በዙሪያዋም ተመላለሱ፥ 
ግንቦችዋንም ቍጠሩ፤ 
በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፤ 
አዳራሽዋን አስቡ፤ 
ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።" 
መዝሙር 48: 12-13

በዊኒፔግ ካናዳ የ2004 ኅዳር ጽዮን በዓል ፎቶዎችን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ!! Click here to view celebration of Hidar Tsion 2011 in Winnipeg, Canada

Tuesday 6 December 2011

የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በዋሻ ውስጥ ተገኘ


ምንጭ አንድ አድርገን ብሎግ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሰማነው እግዚአብሔር አሁንም  አብሮን እንዳለ 

በምህረቱም እየጎበኝን እያለ መሆኑን ነው፤ በጠላት ወረራ ጊዜ የተቀበረውን 
የቅዱስ ገብርኤልን ቤተክርስትያ በማውጣት አሳይቶናል ፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን:: እግዚአብሔር አልተወንም ፤ 
አይተወንም የሚያስብል ተዓምር ነው የተደረገው፡፡ 

Thursday 1 December 2011

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና ታቦተ ጽዮን


ኅዳር 20/2004 ዓ.ም
ዲ/ን ሽመልስ መርጊያ

እግዚአብሔር አምላክ ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ካወጣቸው በኋላ የአምልኮ ሥርዐታትን ይፈጽሙበት ዘንድ የምስክሩን ድንኳን፣ የቃል ኪዳኗ ታቦትንና ለአምልኮ ሥርዐቱ ማከናወኛ የሚያገለግሉ ልዩ ልዩ ንዋያተ ቅድሳትን እንዲሠሩ በሙሴ በኩል ታዘው ነበር፡፡ ከቃል 3p-03ኪዳኗ ታቦት ውስጥም በእግዚአብሔር ጣት ዐሥርቱ ትእዛዛት የተጻፉበት የሕጉ ጽላት፣ አርባ ዓመት ሙሉ እስራኤላውያን በሲና ምድረ በዳ የተመገቡትን መና የያዘች መሶበ-ወርቅ፣ አሮን ለክህነት አገልግሎት ስለመመረጡ ምስክር የሆነችው ለምልማና ፍሬ አፍርታ የተገኘችው የአሮን በትር ይገኙባታል፡፡(ዕብ.9፡4)