Friday 6 January 2012

ነገረ ልደቱ ለክርስቶስ - ዲያቆን መልአኩ እዘዘው የኔነህ


ነገረ ልደቱ ለክርስቶስ

እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!!

በገባው አምላካዊ ቃል መሠረት አዳምን ለማዳን የዘመናት መቆየትየወር 
መጉደል ማለፍ'የቀናት መዛነፍ ሳይኖርበት፤ በቃሉ መሠረት በልበ ሥላሴ 
ታስባ በኖረች ጥንተ አብሶ (የቀደመ በደልካላገኛት፣ በንጽሕናና በቅድስና 
በድንግልናም ተጠብቃ ትኖር ከነበረችው፣ በሕሊና ሥላሴ የማይቆጠር 
ዕድሜ ካላት በሥጋ ግን 15 ዓመት ብላቴና ከሆነች ከንጽሕት ቅድስት 
ድንግል ማርያም ያለወንድ ዘር በብሥራተ ገብርኤል ተጸነሰ፡፡

እንደ ሰው ሥርዓት  9 ወር ቀን በኋላ ንጉስ ነኝ ብሎ ዙፋን ሳይዘረጋ፣ 
ቤተ መንግስት ሳያሠራ፣ ክቡር ነኝ ብሎ ወርቅ ሳይለብስ፣ ሰው በሚኖርበት 
ሳይሆን ከብቶች በሚኖሩበት በበረት ውስጥ በቤተልሔም አውራጃ ተወለደ፡፡ 
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶቤተ-ክርስቲያንም ይህንን የጌታን ልደት 
ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት በመመደብ በድምቀት ታከብራዋለች፡፡ 



አምላክ ለምን ሥጋ ለበሰለምን ተወለደ?
    ሰይጣን አስቀድሞ ከክብሩ በተዋረደበት ‹‹የአምላክነት ምኞት›› 
አዳምንም ፈትኖ ከገነት አስወጥቶታል፡፡ ሰይጣን አዳም ሲፈትን 
የእባብን አካል ተዋሕዶ በእባብ አካል አድሮ ነበር፡፡ አምላካችን 
ይህንን የሠይጣን ጥበብ ተመልክቶ አዳምን ለማዳን ሌላ ጥበብ 
አላስፈለገውም፡፡ ራሱ ሰይጣን በተጠቀመበት ጥበብ አዳምንና ዘሩን 
ሊያድን ሽቶ፤ ሰይጣን የእባብን አካል ተዋሕዶ አዳምን እንዳሳተ 
እግዚአብሔርም የሰውን ልጅ ሥጋ ተዋሕዶ አዳምን ለማዳን ሰው 
መሆን አስፈልጎታል፡፡
አዳም የፈለገውን የተመኘውን አምላክነት ሊሰጠው ሽቶ እግዚአብሔር 
የሰውን ሥጋ ለበሰ፡፡ በዘፍ.3. 22 ‹‹እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን 
ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ›› የሚለው ቃል ከሦስቱ አካላት 
አንዱ ወልድ ሥጋ እንደሚለብስ የሚያጠይቅና በአንጻሩ ደግሞ 
የሰው ልጅ መልካሙንና ክፉውን ለመለየት የሚቻለው አምላክ መሆኑን ያሳያል፡፡
 የተነገረውን ትንቢት ለመፈፀም   በኢሳ. 9.6                                          ‹‹ ህጻን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ                 ነው ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል ›› ያለው በተመሳሳይ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም           ዐማኑኤል ብላ ትጠራዋለች ›› (ኢሳ. 7.14) ተብሎ የተነገረው እንዲሁም በነቢዩ ዳዊት‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም አገኘ ነው ›› በማለት                   የተናገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ አምላክ በድንግል ማኅጸን አድሮ  በጠባቡ የሰው አካል ተወስኖ እንደ ሰው ሥርዓት በቤተልሔም ተወለደ፡፡ ከቦታዎችም መርጦ በቤተልሔም መወለዱ አስቀድሞ በነቢዩ ሚኪያስ ‹‹አንቺ ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ አንቺ በይሁዳ ካሉት መካከል ትሆኝ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ አስቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ በእስራኤልም ላይ ገዢ የሚሆን ይወጣልኛል ›› (ሚኪ.5.2) ተብሎ የተነገረ ትንቢት ስላለ ነው፡፡


  አምላክ ለምን ያለ ወንድ ዘር ተወለደ?

እግዚአብሔር ሔዋንን ሲፈጥራት ከአዳም ጎን ነበር ያስገኛት በመሆኑም ወንዶች እኛ ያለሴት እናንተን ሴቶችን አስገኝተናል እናንተ ግን ያለ ወንድ ልታስገኙን አትችሉም ብለው ይመኩ ነበርና ይህንን ትምክህት ለማራቅ እመቤታችን ያለ ወንድ ዘር እርሱን በፈቃዱ አስገኝታዋለች፡፡

    ሳሙ.7.14  ላይ ‹‹ እኔም አባት እሆነዋለሁ እርሱ ልጅ ይሆንልኛል ››  ተብሎ እንደተጻፈ ለጌታችን ከአብ በቀር አባት የሚስፈልገው አይደለምና እንደ ሰው ሥርዓት እርሱን በመውለድ አባት የሚሆነው አያሻውምና ከድንግል ያለ ዘር ተወለደ፡፡

    ‹‹ልደት ቀዳማዊ ተዐውቀ በደኃራዊ ልደት›› ‹‹ያለ እናት ቅድመ ዓለም የተወለደው ልደት፤ በምድር  ያለ አባት በተወለደው ልደት ታወቀ ›› እንዲል ቀድሞ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ያለ እናት መወለዱን ሊገልጥልን ስለ ወደደ ከእመቤታችን ያለ አባት ተወለደ፡፡


  እግዚአብሔር አዳምን ለማዳን ለምን ፈለገ?

     የመጀመሪያው ምክንያት የአዳም በንስሐ መመለስ ነው እግዚአብሔር የሠዎችን መጥፋት አይወድም ፤ ይልቁን በሐዘን ከስሕተታቸው የሚመለሱትን ይወዳል ያድናል፡፡በኢዮ.2.12 ‹‹ ከሩቅም ሆነው ባዩት ጊዜ አላወቁትም፤ በታላቅ ድምፅም ጮኸው አለቀሱ፤መጎናጸፊያቸውንም ቀደዱ፤ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነሰነሱ›› በማለት እንደተፃፈ፤እንዲሁም በወንጌል ‹‹ ይህ ልጄ ሞቶ ነበር፤ አሁን ግን ሕያው ሆኖአልና ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልና ›› (ሉቃ. 16.24) ተብሎ እንደተጻፈው እግዚአብሔር የሰዎችን ከጥፋት መመለስ እንጂ ጥፋትን አይሻምና ነው፡፡
    
ሁለተኛው ደግሞ በደል ክፋት የአዳም ተፈጥሮ ወይም ባሕርይ አይደለምና ከባሕርይው ውጪ የሆነውን ነገረ ሊያርቅለት (ሊያድነውአምላክ ስላሰበ፣ ፍጠረኝ  ሳይለኝ  ፈጥሬዋለሁና መዳንም በፈለገበት ጊዜ ላድነው ይገባኛል ብሎ ከፍቅር የተነሣ  ሊያድነው ወደደ፡፡


ዓለምን የማዳን ጥበብ ዓለምን ከመፍጠር ጥበብ 
እንዴት ይበልጣል ( ይረቃል) ?

የአንበሳ ሥጋ መብላት፤ የአህያ ሣር መጋጥ፤ የበሬ መዋጋት የሚያስደንቅ አይደለም የተለመደ ነውና:: የሰው መሞት አያስደንቅም የሰው ማረግ  ግን ያስደንቃል፣ያስደምማል እንግዳ ነገር ነውና፡፡ ፈጣሪ  ፍጥረታትን በተለያየ አኳኋን ቢፈጥር አያስደንቅም ምክንያቱም ፈጣሪ መፍጠር የሚቻለው ሁሉን ማድረግ የማይሳነው ነውና::  እግዚአብሔር በአምላክነቱ ሁሉ ይቻለዋልና:: ሟች ፈራሽ በስባሽ የሆነ ሰው ደግሞ መራብ'መጠማቱመሞቱ የሚያስደንቅ አይደለም፡፡ ለእኛ የተለመደ የባሕርይ ገንዘባችን ነውና፡፡ነገር ግን ሰውን የአምላክን ሥራ ሲሰራ ቢያዩት ያስደንቃል፣ ያስደምማል፡፡ 

ሰው በዘላለማዊው የእግዚአብሔር ዙፋን ሲገለጥ በየማነ አብ (በአብ ቀኝበዘባነኪሩብ (በኪሩብ ጀርባሲቀመጥ ማየት ድንቅ ጥበብ ነው፡፡ በአንጻሩ ደግሞ የማይሞተውን፤ ሞትም የማይስማማውን ሲሞት ማየት በአንደበት ከመግለጽ በላይ የሆነ ድንቅ ነገር ነውና እግዚአብሔር ሞትንና ሲዖልን ዲያቢሎስን በሥልጣኑ ሳይሆን በሞቱ ድል ይነሳ ዘንድ የአዳምን ሥጋ መልበስ መወለድ ነበረበት፤ ስለዚህም ነው ‹‹ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበብ ይበልጣል›› የተባለው፡ 


አምላክ በመወለዱ(ሰው በመሆኑምን ተጠቀምን?

   
ሰው አምላክ ሆነአምላክ ሰው በሆነ ጊዜ ሰው አምላክ ሆኗል፡፡ መለኮት ሥጋን ሲዋሐድ ረቂቁ  ገዘፈ ምሉዕ የሆነው መለኮት ተወሰነ፤ሥጋም መለኮትን ሲዋሐድ ግዙፉሥጋ ረቀቀ የተወሰነው (የተገደበውሥጋ ምሉዕ (በሁሉ ያለሆነ ፍጡሩ አመስጋኙ ሥጋ ፈጣሪ የሚመሰገን ሆነ፡፡

ከዲያቢሎስ ቁራኝነት ተላቀቅን፡- ከአዳም በደል ጀምሮ ዲያቢሎስ የሚወለዱ ህጻናትን በእናታቸው ማኅጸን በዘር ምክንያት እየተቆራኘ ጥንተ አብሶ (የቀደመው በደልተብሎ ከልጅ ልጅ ሲተላለፍ የቆየውን የባርነት ቀንበር አምላክ ያለ ወንድ ዘር በመወለድ ይህንን የዲያብሎስ ቁራኝነት አራቀልን፡፡ ከሞት ከኩነኔ፤ ከፍዳ ከመርገም፤ ከሲኦል ከገሃነም፤ከዲያቢሎስ ወጥመድ ከኃጢአት እኛ ልጆቹን አዳነን፡፡

አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት ሥልጣን ተሠጠን ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹የአብርሃምን ዘር ይዟል እንጂ የያዘው የመላእክትን አይደለም ›› ወይም የሥጋን ባሕርይ አምላክ ገንዘብ አድርጓልና እንደ ቀድሞው አርቀን ‹‹ፈጣሪያችን፤አምላካችን›› ብለን ሳይሆን የምንጠራው ‹‹አባታችን ›› ብለን አቅርበን እንጠራዋለን፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ለተቀበሉት ሁሉ ግን በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድሥልጣንን ሰጣቸው ›› (ዮሐ.1.12) በማለት እንደተናገረ፡
መምህረ ትሕትና ወፍቅር መድኃኔዓለም 
ከብርሃነ ልደቱ ረድኤት በረከት ያሳድርብን አሜን


                                        !!ወስብሐት ለእግዚአብሔር

No comments:

Post a Comment