Thursday 12 January 2012

ምሥጢረ ሥላሴ - ዲያቆን መልአኩ እዘዘው


         ምሥጢረ ሥላሴ






እንኳን ለጥር ሥላሴ በዓል 
በሰላም አደረሳችሁ!!

ምሥጢር
አመሠጠረ ከሚለው ግስ የተገኘ ቃል ሲሆን ስውር  ድብቅ  
ሽሽግ ማለት ሲሆን አምስቱአዕማደ ምሥጢራትም ምሥጢር 
የተባሉበት ምክንያት
  • በሥጋዊ ጥበብ ምርምር መረዳት ስለማይቻሉ
  • ላመኑት እንጂ ላላመኑት ሰዎች የተሰወሩ በመሆኑ
 ምሥጢር በሁለት ይከፈላል፡፡ እነርሱም፡-
 የፈጣሪ ምሥጢር- ሊገለጥ የማይችል ነው፡፡  እስከ የሌለው ምሥጢርም 
ይባላል፡፡
 የፍጡራን ምሥጢር- በጊዜ የሚገለጥ /የሚታወቅነው፡፡ 
የሰውና የመላእክትምሥጢር በዚህ ውስጥ የሚካተት ነው፡፡

ምሥጢረ ሥላሴ
ሥላሴ- የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስትነት ማለት ነው፡፡ እግዚአብሔር አንድ ሲሆን 
ሦስት ሦስት ሲሆን አንድ ነው፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ሦስትነት ልዩ ሦስት ነው፡፡ 
ሦስት ብቻተብሎ አይቆምምና ሦስት ሲሆን አንድም ነው፡፡ 
ስለዚህ እግዚአብሔር የአንድነትየሦስትነት ባለቤት በመሆኑ ሥላሴ ይባላል፡፡
 የእግዚአብሔር አንድነት
 እግዚአብሔር አንድ ነው ስንል በመለኮት  በባሕርይ  በአገዛዝ   
በሥልጣን  በሕላዌ/ሕልውናበመፍጠር በልብ በቃል በእስትንፋስ 
ይህን ዓለም በመፍጠር እና በማሳለፍይህን በመሳሰለው ነው፡፡

  በመፍጠር መዝ 10125  ዘፍ 1 ኢሳ 661-2 
  በሥልጣን ዮሐ 1030 
  በመለኮት መለኮት ማልኩት ከሚለው የዕብራይስጥ ቃል የተገኘ ሲሆን 
መንግስት ግዛትማለት ነው፡፡ ይህም ለእግዚአብሔር ብቻ የተሰጠ ነው፡፡ 
ቆላ 29 1 ጴጥ 13 
  በሕላዌ /ሕልውና/  አኗኗር ማለት ነው፡፡ መብለጥ  
መቅደም  መቀዳደምየለባቸውም፡፡ ዮሐ 11-2 ዮሐ 1410 
ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የውስጥ ገጽታ
የእግዚአብሔር ልዩ ሦስትነት
 እግዚአብሔር በስም፣ በአካል፣ በግብር ሦስት ነው፡፡
 የስም ሦስትነት አብ ወልድ መንፈስቅዱስ ናቸው፡፡ ማቴ 2819፡፡
እግዚአብሔር አብ- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት 
የአንዱ የአብ ስም ነው፡፡1 ጴጥ 12 ዮሐ 316
እግዚአብሔር ወልድ- ከዘለዓለም እስከዘለዓለም ከሦስቱ አካላት 
የአንዱ የወልድ ስምነው፡፡ ወልድ ሰው በሆነ ጊዜ በተለያ ስሞች ተጠርቷል፡፡
 እነዚህም፡-
        ኢየሱስ- መድኃኒት አዳኝ ማለት ነው፡፡ ማቴ 121
         ክርስቶስ- መሲሕ /ንጉሥማለት ነው፡፡ ሉቃ 211 ዮሐ 425
         አማኑኤል-እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው ማለት ነው፡፡ 
ትን.ኢሳ 714    ማቴ121

እግዚአብሔር ወልድን አምላክነት አስረጂ 
የሆኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች
ዮሐ 20 ሮሜ 1012  ዮሐ 1 ዮሐ 114  
ዮሐ 2028  ዮሐ442  የሐዋ.ሥራ 2028  ራዕይ 1 
ትን.ኢሳ 9 ራዕይ 2212 ፡፡
 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ፡- ከዘለዓም እስከ ዘለዓለም ከሦስቱ አካላት 
የአንዱ መንፈስ ቅዱስ ስሙ ነው፡፡
 መንፈስ ቅዱስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡
  • መንፈስዮሐ 3 1 ቆሮ 12 ዘፍ 1 ትን.ኢሳ 4816
  • የእግዚአብሔር መንፈስ - .ኢሳ 616
  • ጰራቅሊጦስ /አጽናኝእየተባለ ይጠራል፡፡ ዮሐ 1526  ዮሐ 1416  ዮሐ167
  • የእውነት መንፈስ፡፡ ዮሐ 1526

የአካል ሦስትነት
    ለአብ ፍጹም ገጽ  ፍጹም መልክ  ፍጹም አካል አለው፡፡
    ለወልድም ፍጹም ገጽ  ፍጹም መልክ  ፍጹም አካል አለው፡፡
    ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም ገጽ  ፍጹም መልክ  ፍጹም አካል አለው፡፡
የግብር ሦስትነት
የአብ ግብሩ መውለድ ማስረጽ  የወልድ ግብሩ መወለድ  የመንፈስ ቅዱስ ግብሩመስረጽ ነው፡፡ አብ ወልድን ውልዷል  መንፈስ ቅዱስን አስርጽዋል  መንፈስ ቅዱስከአብ ሰርጽዋል፡፡ ወልድ ከአብ ተወልዷል ፡፡

  • አብ ወልድን ወለደ ማለት  ከአካሉ ከባሕርይው  አስገኘው ማለት ነው፡፡
ምሳሌ የሰው ነፍስ ልብነቷ /አሳቢነቷቃልነቷን እንደሚያስገኘው

  • ወልድ ከአብ ተወለደ ማለት  አብን አክሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለትነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ቃልነቷ ከልብ እንደተገኘ

  • አብ መንፈስ ቅዱስን አሰረጸው ማለት  ከአካሉ ከባሕርይው አስገኘው ማለትነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ ልብነቷ እስትንፋስነት /ሕይወትነቷንእንዳስገኘ ማለት ነው

  • መንፈስ ቅዱስ ከአብ ሰረጸማለት  አብን አህሎ አብን መስሎ ከአብ ተገኘ ማለትነው፡፡
ምሳሌ የነፍስ እስትንፋስነቷ ከልብ እንደተገኘ

 ይህ ማለት ግን መቀዳደም ፤ መበላለጥ አለባቸው ማለት አይደለም ፡፡
ጎንደር ደብረብርሃን ሥላሴ ቤተክርስቲያን የውጭ ገጽታ

ለምሥጢረ ሥላሴ የፍጡራን ምሳሌ

የሰው ነፍስ፡- የመናገር  የማሰብ ፣የመተንፈስ /የሕያውነትሁኔታ አላት፡፡
ማሰብ በአብ  መናገር በወልድ  ሕያውነት በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላሉ፡፡
የነፍስ ልብነቷ ቃልነቷን ሕይወትነቷን ከራሷ ታስገኛለች፡፡
ነፍስ ስትገኝ በሦስትነቷ በአንድ ጊዜ ተገኘች እንጂ ልብነቷ ቀድሞ 
ቃልነቷ እስትንፋስነቷበኋላ አልተገኘም፡፡ ነፍስ በኩነታት ሦስትነት 
ቢኖራትም በአካል አንድ ናት፤ ሥላሴ ግንአብ አካላዊ ልብ፤ 
ወልድ አካላዊ ቃል  መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ ነው፡፡

ፀሐይ፡አንድ ስትሆን ሦስትነት አላት፡፡ አካሏ  ብርሃኗ   
ሙቀቷ ናቸው፡፡ አካሏበአብ፣ ብርሃኗ በወልድ፣ ሙቀቷ 
በመንፈስ ቅዱስ ይመስላል፡፡

ባሕር- ስፋቱ በአብ፣ ርጥበቱ በወልድ  
ማዕበሉ በመንፈስ ቅዱስ ይመሰላል፡፡

ስለ ምሥጢረ ሥላሴ የማገናዘቢያ ጥቅሶች ፡-

            በብሉይ ኪዳን     
.ኢሳ 4812  መዝ 11716 ዘኁ 624  
ዘፍ 322 ፣ት.ኢሳ 6

            በሐዲስ ኪዳን
1 ቆሮ 1914  ማቴ 1715  ሉቃ322  ማቴ 2819 
 ማቴ 316  ዩሐ16 የሐዋ.ሥራ 755  ዮሐ 1415  ራዕይ 141-2

በዓሉን በዓለ ሰላም ፤ በዓለ ክብር ፤ በዓለ ፍስሐ ያድርግልን - አሜን!!

No comments:

Post a Comment