Wednesday 25 July 2012

ቁልቢ ገብርኤል



ቁልቢ ገብርኤል



ዲያቆን መልአኩ እዘዘው

 ከአዲስ አበባ በስተምሥራቅ 461/ርቀት ላይ በምዕራብ ሐረርጌሀበገረ ስብከት
 ጋራ ሙለታ የሚገኝ ቤተክርስቲያን ነው፡፡ የዚህን ደብርአመሠራረት በተመለከተ 
በብዙ ሊቃውንትየሚተረከው የሚከተለው ነው::በዘጠነኛው //ዮዲት ጉዲት
ተነሥታ አብያተ ክርስቲያናትንስትመዘብር፣ ክርስቲያኖችን ስትገድልና
መጻሕፍትን ስትቆነጻጽል ንጉሥ አንበሣ ውድም በአኩስምና በአከባቢዋ የነበሩ 
ታቦታትንና ንዋያተቅዱሳትን በመያዝ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ዝዋይ መጣ፡፡


40 ዓመታት ስደት በኋላ አንበሣ ውድም ወደ አኩሱም ሲመለስና የንዋያተ ቅዱሳት
 ቆጠራሲደረግ ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በዝዋይ መቅረቱ ታወቀ፡፡ ከኤርትራ ደብረ ሲና 
ማርያም የመጡትአባ ሌዊ የተባሉ አባት ታቦቱን ለማምጣት ከንጉሡ አስፈቅደው 
ወደ ዝዋይ መጡ፡፡

አባ ሌዊ ከሰባት ቀን ሱባኤ በኋላ ታቦተ ቅዱስገብርኤልን ይዘው ወደ አኩሱም
 ሲጓዙ ቅዱስገብርኤል ተገልጦ “እኔ ወደማሳይህ ቦታ ታቦቱን ይዘህሂድ” አላቸው፡፡
 አባ ሌዊም ታቦቱን ይዘውተከተሉት፡፡ በመጨረሻም ቁልቢ ደረሱ፡፡ ለአባ ሌዊም
የተፈቀደላቸው ቦታ ይሄ መሆኑን ታቦቱም በኋላ ዘመንለሕዝቡ ድንቅ ሥራ 
እንደሚሠራ ቅዱስ ገብርኤል ነግሯቸው ተሠወረ፡፡ 
አባ ሌዊ በቦታው 130ዓመታት ያህል አገልግለው በንጉሥ ግርማ ሥዩም 
ዘመነ መንግሥተ ታኅሳስ 14 ቀን ዐርፈዋል፡፡
ግራኝ አሕመድ ኢትዮጵያን ሲወርር ብዙ ካህናትከሰሜን ኢትዮጵያ ታቦታትንና
 ንዋያተ ቅዱሳትን ይዘውሲጓዙ ቁልቢ ደረሱ፡፡ መልአከ ገነት መብረቁ፣ 
መምህርየማነ አብ፣ አባ ተከስተ ሥሉስ የተባሉ ካህናትከተነጠፈድንጋይ ላይ 
የተጻፈ ድንጋይ ላይ የተጻፈ ነገር ያገኛሉ ጽሑፉም ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል በሥዉር 
መቀመጡን፣ልዩ ልዩ ተአምራት እንደሚፈጸምበት፣ ወደ ፊትም ታላቅ
ቤተ መቅደስ እንደሚሠራበት፣ እንዴት አባ ሌዊ ታቦቱንወደዚህ ቦታ እንዳመጡት
 የሚገልጽ ነበር፡፡ እነርሱም ይህን ታሪክ ይዘውት በነበረው መጽሐፈ ቀሌሜንጦስ
ሕዳግ ላይ ጻፉት፡፡ ወደ ዝዋይ ሴት ሲደርሱምመጽሐፉን በዚያ አኖሩት፡፡
ልዑል ራስ መኰነን ከዝዋይ ደሴት መጽሐፈ ቀሌሜንጦስን አስመጥተው ሲያነቡ 
የቁልቢ ገብርኤልን ታሪክ በማግኘታቸው የቅዱስ ገብርኤልን ቤተ ክርስቲያን ለማነጽ 
ተነሡ፡፡ ልዑል ራስ መኰነን በአከባቢው የአየር ንብረት ተማርከው በሥፍራው ቤት 
ሠርተው ነበር፡፡ ልዑል ራስመኰነን ቁልቢ ገብርኤልን ከመትከላቸው በፊት ቦታው 
የአከባቢው ጎሳዎች የግጭት መነሃርያነበር፡፡ ሰላምን በአከባቢው ከመሠረትህ በቦታው
 በስምህ ቤተ ክርስቲያን እሠራልሃልሁ ብለውእንደተሳሉም ይነገራል፡፡
የተሳሉት በመፈጸሙ የቅዱስ ገብርኤል ታቦት የት እንዳለ ሲያፈላልጉ ቡልጋ ውስጥ
ከአዠጉጉ ካህናተ ሰማይ ጋር አባ ዱባለ የተባሉ ካህን ያስቀመጡት ታቦተ ቅዱስ ገብርኤል 
መኖሩተነገራቸው፡፡ ልዑል ራስ መኰንን ለአባ ዱባለ መልእክት ስለላኩባቸው ከሐረር 
በተላኩ ካህናትአማካኝነት የቅዱስ ገብርኤልን ታቦት ላኩ፡፡ ልዑል ራስ መኰንንም 
ከነሠራዊቶቻቸው ሸንኮራ ድረስ ሄደው ታቦቱን በመቀበል የካቲት 21 ቀን 1884 .
 ታቦቱ ቁልቢ ገባ፡፡ የመቃኞው ሥራ 1883 . ተጀምሮ ፍጻሜ አግኝቶ 
ቅዳሴ ቤቱ የተከበረው ሐምሌ 19ቀን 1884 . ነው፡፡ በዚሁ ዕለት የዋናው 
ቤተ ክርስቲያን ሕንጻ ሥራ የመሠረቱ ድንጋይ ተጥሎ ታኅሳስ 19 ቀን 1888 . 
የቤተ ክርስቲያኑ ሥራ ተፈጽሞ በአቡነ ማትያስ ተባረከ፡፡ ቦታው ከባለ አባቶች የገዙት 
በአርባ የቁም ከብት ነው፡፡ ራስ መኰንን መጋቢት ዘጠኝ ቀን 1889 . 
ወደ አዲስ አበባ ሲሄዱ እዚህ ቦታ ላይ በድንገት ስለታመሙ በዕለቱ ሥጋ ወደሙ 
ተቀብለውበታል፡ በመጀመርያ ሲተከል በገጠር ቤተ ክርስቲያን ሥሪት ሲሆን በኋላ ግን
በስእለት ሰማኢነቱ በመላ ኢትዮጵያ እየታወቀ ስለ መጣ ደብር ሆኗል፡፡
የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና በረከት አይለየን!!


No comments:

Post a Comment