Tuesday 6 December 2011

የቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን በዋሻ ውስጥ ተገኘ


ምንጭ አንድ አድርገን ብሎግ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ የሰማነው እግዚአብሔር አሁንም  አብሮን እንዳለ 

በምህረቱም እየጎበኝን እያለ መሆኑን ነው፤ በጠላት ወረራ ጊዜ የተቀበረውን 
የቅዱስ ገብርኤልን ቤተክርስትያ በማውጣት አሳይቶናል ፡፡
እግዚአብሔር ይመስገን:: እግዚአብሔር አልተወንም ፤ 
አይተወንም የሚያስብል ተዓምር ነው የተደረገው፡፡ 


ይህ ጥንታዊ ዋሻ በውስጡ አካቶ ይዟቸው የሚገኝው አስደናቂው ነገር 
ርዝመቱ በውል ያልታወቀ የግብር ቤትና ፤ የክርስትና ቤት በውስጡ የሚገኝ ሲሆን ፤
 ከኢጣልያን ወረራ እና ከግራኝ መሀመድ በመሸሽ የተቀበረ ቅርስና ፅላት ተገኝቶበታል፡፡ 
ይህንን ጥንታዊ ዋሻ ያገኙት አባት በራዕይ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ፅላት
 በውስጡ እንዳለ ተነግሯቸው ቁፋሮ ለመጀመር በሱባኤ ላይ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል፡፡ 
ሌላው አስደናቂው ነገር ከዋሻው መካከል ላይ የብርሀን መግቢያ የተፈጥሮ ክፍተት 
ያለው መሆኑ ድንቅ ያሰኛል፡፡ የዋሻው ጠረጋ ሲጀመር የአባቶች አፅም ፤ 
የብራና መፃህፍት ፤ የፅንአ ቁርጥራጭ ፤ የሰም ስብርባሪ በውስጡ እንደተገኝ 
ለማወቅ ችለናል፡፡ 


በተጨማሪም  በዋሻው የውስጥ ክፍል ቅኔ ማህሌት ፤ ቅድስት ፤ መቅደስና ቤተልሔም 
ይገኙበታል ::
 ለመላው ህዝበ ክርስትያን በሙሉ አስደናቂውን እና ተዓምረኛውን የዋሻ ገብርኤል 
ቤተክርስትያን በአቃቂ ቃሊቲ ከቶታል ሳሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስትያን 
ወረድ ብሎ መብራት ሀይል ማዶ ላይ የተገኘውን የጥንት ዋሻ ቤተክርስትያን 
ብዙ ገቢረ ተዓምራ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህውም በፀበሉ ፤ በእምነቱ ፤ 
በንፍሮ ውሀው ብዙ ህሙማና አጋንንት እየፈወሰ ስለሚገኝ በቦታ ተገኝተው 
ከበረከቱ እና ከገቢረ ተዓምሩ ተካፋይ በመሆን የቦታውን ታሪክም በአካል 
እንዲያዩ በቅዱስ ገብርኤል ስም ጥሪያችን እናስተላልፋለን፡፡ 
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከሳሎ ጊዮርጊስ ወረድ ብሎ መብራት ሐይል ማዶ ገላን ጉዳ መተሊ ቅዱስ አሮንና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስትያን
 ለበለጠ መረጃ 0913-464936 ደውለው የተሻለ መረጃ ማግኝት ይችላሉ

 ‹‹እግዚአብሔር ቤተክርስትያናችንን ይጠብቅ››

2 comments:

  1. betam des yila ahun getachen amlakachen esu egziabher betekrstiyann kemezegat adnon enbarek zend yikfetln

    ReplyDelete
  2. egziabhier yestelgn kale hiwot yasemalign.

    ReplyDelete