Saturday 25 June 2011

የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተሰርታ ያለቀች ናት

"… በአሁኑ ጊዜ ያለው አገልግሎቱ እየተዳፈነ አገልጋዮቹ እየወጡ ከአገልግሎቱ ይልቅ አገልጋዮቹ እየታወቁ ነው ከወንጌሉ ይልቅ ወንጌላውያኑ … የአንድ አገልጋይ ስራ ሕዝቡን ከክርስቶስ ጋር ማገናኘት ነው አሁን …ሕዝቡ ወደእኛ ነው የሚመጣው … እግዚአብሔርን አያገኝም፡፡ አንድ ጳጳስ አንድ ሰባኪ አንድ መነኩሴ አንድ ዘማሪ ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጣ የግል ሃሳቡን ቤተክርስቲያን ላይ ሊጭን ሳይሆን ሃሳቧን ተቀብሎ እንደ ቧንቧ ለሕዝብ ሊያዳርስ ነው፡፡ … ቤተክርስቲያንን ካህን ቤተመንግስትን ወታደር ነው የሚደፍረው …ሰው ራሱን መለወጥ ሲያቅተው ሥርዐት ለመለወጥ ይታገላል ራሱን ማደስ ሲያቅተው ሃይማኖትን ለማደስ ይታገላል፡፡ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተሰርታ ያለቀች ናት ተሰርቶ ባለቀ ቤት ገብቶ መኖር እንጂ ይቀየር የማለት መብት የለህም በዝቷል ይቀነስ ረዝሟል ይጠር ተጣሟል ላቃና የሚባል ነገር የለም፡፡ ቤተክርስቲያን ሰውን ታድሳለች እንጂ ሰው ሊያድሳት አይችልም፡፡ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማት አሁን ተሃድሶ ያነጣጠረባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡ ከመንፈሳዊ ኮሌጅ የሚወጡ ናቸው መምህር ካህን መነኩሴና ጳጳስ የሚሆኑት እነዚህን ከያዝን በቃ ቤተክርስቲያኑን ተቆጣጠርን በሚል ሥርዐተ ትምህርቱን ጉዳት እያደረሱበት ነው፡፡ አንዳንዶቹን መምህራን ሲችሉ በጥቅም እየገዙ ደቀመዛሙርቱ ከሀገረ ስብከት ሲላኩ ሆነ ተብሎ በዚህ ደረጃ እንዲመረጡ እያደረጉ ነው … አንድ ስብከት ኦርቶዶክሳዊ የሚባለው ክርስቶስን ግንድ ቅዱሳንን ጻድቃን ሰማዕታትን ቅርንጫፍ አድርጎ ብሉይን ሓዲስን መጻህፍተ ሊቃውንት መጻህፍተ መነኮሳትን መሰረት የሥራ መጻህፍትን ቅርንጫፍ አድርጎ መስበክ ሲችል ነው ይሄን መስበክ ካልቻለ ችግር አለበት ማለት ነው፡፡ …ተሃድሶ ቤተክርስቲያኒቱን ፕሮቴስታንታዊ የማድረግ ስልት ነው፡፡ "



መጋቤ ሐዲስ እሸቱ አለማየሁ ስለ ተሃድሶ … (በአዲስ ጉዳይ መጽሔት ሰኔ 2003)



No comments:

Post a Comment