Tuesday 7 June 2011

New Great Ethiopian Orthodox Mezmur By Zemarit Azeb.....(Tewahedo)

ተዋህዶ ሀይማኖቴ
የጥንት ነሽ የእናትና አባቴ
ማህተቤን አልበስም
ትኖራለች ለዘለአለም

የግብጽን ከተሞች በደንም ገንብተናል
በመግደል ጽድቅ የለም ሞትን ግን ኖረናል
ማህተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ
እኔስ ከእነ አንገቴ ውስዱት አልሁኝ

ጴጥሮስ ተሰቀል ጳውሎስ ተሰየፈ
ተዋህዶ እያለ እረ ስንቱ አለፈ
ሌሎችም በእሳት በስቃይ አልፈዋል
ዘመን የማይሽረው ታሪክን ጽፈዋል

ፈተኛ ነንና እንዳንሆን ሐለኛ
ህዝቤ ተነቃቃ ተነሳ አትተኛ
ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን
እንዳይሆን ተረቱ
የተዋህዶ ልጆች አሁን ነው ሰአቱ


አይተን እንዳላየን ስንት አሳልፈናል
የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል
አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር
ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ክብር

1 comment:

  1. ejig betam des yemil gitim ena mezmur. zimare Melahiktn yasemalin

    ReplyDelete